Get Mystery Box with random crypto!

~ ርቱዕ ተፈጥሯዊ ሕግ ~ (the natural law) ~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

~ ርቱዕ ተፈጥሯዊ ሕግ ~ (the natural law)

~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~
                      ምን ዓይነት ሕግጋት ናቸው ~?

ክፍል-2

ርቱዕ ተፈጥሯዊ ሕግ ፦ (the natural law) ደግሞ የወንጌል ሕግ እስኪሰጥ ድረስ መዘጋጃ ሆኖ የተሰጠ እና ሰዎች ፍትሕን እና የክፋት ውጤትን በመፍራት መልካምነትን እየተከተሉ ይ'መሩበት ዘንድ(በዋናነት በሙሴ አማካነዠኝነት ለአብርሃም ልጆች ለእስራኤላውያን)የተሰጠ ሕግ ነው። ይህ ርቱዕ(ፍትሕ ያለበት)ሕግ ነው።
ይህ ሕግ ሰው የገደለ ራሱም ይገደል የሰረቀ እጁ ይቆረጥ ዓይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ ወ.ዘ.ተ የሚሉ ትዕዛዛትን የያዘ ሰዎች በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ጭምር የሚያጋጥማቸውን ቅጣት በመፍራት ሕግጋትን እንድያከብሩ ለማድረግ የተሰጠ የኦሪት ሕግ ነው።ዓለማውያን ሕግጋትም ወደዚህ ሰለሚቀርቡ አል-ኪንዲ ተፈጥሯዊ ሕግ(natural law) ይለዋል።

የሁለቱንም በሙሴ እና በክርስቶስ የተሰጡ ሕግጋት ግኑኝነት በማብራራት በክርስቶስ ሰው መሆን የተሰጠው የወንጌል ሕግ ከኦሪት ሕግ ይልቅ ፍጽምና ያለው በመሆኑ የወንጌሉ ሕግ የቀደመውን የኦሪት ሕግ ፍጹም አድርጎታል ከወንጌል በኋላ እንደገና ወደ ኦሪት ሕግ መመለስ አይገባም-ክርስቲያን ሊቃውንት ከእነዚህ መካካል የፓትርያርክ ጢሞቴዎስ ሐተታ ተጠቃሽ ነው።
ጢሞቴዎስ የቀደመው የኦሪት ሕግ(ተውራት) ምድራዊ ነገሮች ይበዙበት የነበር እና በክርስቶስ ሰው ሆኖ መምጣት ስለሚሰጠው ሰማያዊ ጸጋ የተስፋ ትንቢት የተነገረበት እንደነበር ያስረዳል።

በክርስቶስ የተሰጠች ወንጌል የዚህ ተርፋ ፍጻሜ ስለሆነች ሰማያዊ ጸጋ እና ፍቅርን የምታዝዝ እንጂ እንደ ኦሪት ምድራዊ አስተዳደርን የጦርነት ገድልን ሥጋዊ ሥርዓቶችን የምታዝዝ አይደለችም።

በመሆኑም የእግዚአብሔር ሕግጋት አሠራር(ከኦሪት ወደ ወንጌል የተደረገው ጉዞ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከጊዜያዊ ወደ ዘላለማዊ እሴቶች የተደረገ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ስለ ምድራዊ ነገሮች ወደ ሚወስድ ሕግ መመለስ አይገባም ይህ ከእግዚአብሔር አይደለም እግዚአብሔር ያስጀመረውን ጉዞ ያስጨርሳል እንጂ ቀዠወደ ኋላ አይመልስምና-ይላል ጢሞቴዎስ።

በ15ኛው መ/ክ/ዘመን የተነሱ ስፔናውያን የምዕራብ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትም ተመሳሳይ ሐሳብ አንሥተዋል። ከእነዚህ አንዱ ጴጥሮስ አልፎንሲ እንደሚለው የእስልምናው ነብይ ሙሐመድ የእስልምናን ሕግ ያዘጋጀው ተወግዘው ወደ ዐረብ የሸሹ ክርስቲያን መናፍቃን እና አይሁድ እያማከሩት እንደሆነ ጽፏል።በመሆኑም ሁሉም የራሳቸውን አስተምህሮ የሚያንጸባርቅ አስተምህሮ በማስገባታቸው የእስልምና ሕግ የክርስትና እና የሚሙሴ ሕግ ቅልቅል እንደሆነ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ በሁለቱ መካካል የቆመ እንደሆነ ያትታል።

ይቀጥላል ........

(~የልቦና ችሎት~ "በረከት አዝመራው")