ቀጣዩ የጥናት ክፍል .. ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር አድልዎ ያደርጋልን? በፍጹም አያደርግም! ¹⁵ ለሙሴ፣ “የምምረውን እምረዋለሁ፤ ለምራራለትም እራራለታለሁ” ይላልና። ¹⁶ እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። ¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲነገር ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና። ¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነድነዋል። ሮሜ 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዓመፃ አለ ወይ? አይደለም። ¹⁵ ለሙሴ፦ የምምረውን ሁሉ እምረዋለሁ ለምራራለትም ሁሉ እራራለታለሁ ይላልና። ¹⁶ እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። ¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና። ¹⁸ እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል። -------------- 162 viewsedited 09:44