Get Mystery Box with random crypto!

ሂዳያ - هداية - Islamic Guidance

የቴሌግራም ቻናል አርማ zadulilm — ሂዳያ - هداية - Islamic Guidance
የቴሌግራም ቻናል አርማ zadulilm — ሂዳያ - هداية - Islamic Guidance
የሰርጥ አድራሻ: @zadulilm
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.84K
የሰርጥ መግለጫ

👇Join&and share√
https://t.me/joinchat/AAAAAEAEmxlhmVhRYoDZCw
🔻Contact us @abusemha

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-25 17:39:23
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱሏህ
ቁርአን ለመሐፈዝ የምትፈልጉና የተለየ ክትትል የምትፈልጉ የቁርአን ሒፍዝ መንገዶቹን እና ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች በኦንላይን በቋሚ ትምህርት መልኩ ለመከታተል የምትፈልጉ ወንድም እና እህቶች በተከታዩ ቁጥር በቴሌግራም መመዝገብ ትችላላችሁ።

+251944-22-22-06

https://t.me/alqalamarabic
1.3K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 20:07:22 በአቡ ዐብዱራህማን ኢብራሂም ሲሳይ የሚዘጋጁ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻናል።
• القناة الرسمية لأبي عبد الرحمن إبراهيم بن سيساي فيها دروس ومقالات متنوعة باللغة
الأمهرية
https://t.me/+RELeeXHdY2MQug5s
1.5K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 20:06:40 የኡሱሉ ሰላሳ ማብራሪያ

Explanation of Three Essays on Tawheed three assets 

ክፍል አስራ አራት

አቡ ዐብዱራህማን ኢብራሂም

https://t.me/abu_abdurahman5
በዩቲዩብ
http://youtube.com/channel/UC_mgMFL-R4gC0Lsl5UIDVtg
1.2K views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-13 07:21:05 Watch "አስለቃሾቹ ቀልዶች || አቡ ዐብዱራህማን ኢብራሂም || #SOMI || #SEMHA MEDIA" on YouTube


1.3K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 19:10:53 ቀልድ በኢስላም

የኢስላም የተፈጥሮ ሀይማኖት እንደመሆኑ ተፈጥሮአዊ የሆነውን የሰው ልጅ የመሳቅና የመዝናናት ዝንባሌ አይጋፋም። እንደውም በተቃራኒው ህይወትን ደስተኛና ውብ የሚያደርጉ ነገሮችን ይቀበላል። ሙስሊሞች ተግባቢ፣ ተጫዋችና ፈገግተኛ እንዲሆኑም ያዛል። ፈገግታው የጨለመ፣ ህይወትን ድርቅ ባለና በጨለመ እይታ የሚመለከት ስብእናንም አይወድም።

የሙስሊሞች የመጀመሪያው ተምሳሌት ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ናቸው። የተለያዩ ሀሳቦች፣ ጭንቀቶችና ሀላፊነቶች ቢኖርባቸውም ይቀልዱ ነበር። ይሁን እንጂ ከእውነት ውጪ አይናገሩም። ከባልደረቦቻቸው ጋር ሲኖሩም ተአምራዊና ተፈጥሮአዊ ህይወትን በአንድነት ገፍተዋል። ቀልዳቸውን፣ ጨዋታቸውንና ወጋቸውን ይጋሯቸዋል። ህመማቸውን፣ ትካዜያቸውንና ሀዘናቸውን ይካፈሏቸዋል። ስለመልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሲያወሩ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላሉ፡- “እኔ ጎረቤታቸው ነበርኩ። ወህይ ሲወርድባቸው ይልኩብኛል፤ እጽፍላቸዋለሁ።ስለዱንያ ስናወራ አብረውን ያወራሉ። ስለ አኼራ ስናነሳ አብረውን ያነሳሉ። ስለምግብ ካወጋን አብረውን ያወጋሉ።” (ጠበራኒይ ዘግበውታል።)

ሌሎች ባልደረባዎቻቸው እንደሚሉትም መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከማንም በላይ አስቂኝ ሰው ነበሩ። “ከንዙል ዑምማል” የተሰኘው መጽሀፍ ላይ አንደተጠቀሰው አንዳንዴ ባለቤቶቻቸውን ሲያጫውቱና ዚያዝናኑ እናስተውላለን። ወጎቻቸውንና ተረቶቻቸውን ያደምጧቸዋል። ቡኻሪይ ከእናታች አኢሻ የዘገቡትን የኡሙ ዘርዕን ሀዲስ እዚህ ላይ ዋቢ ማድረግ ይቻላል።

አንዲት ባልቴት ወደርሳቸው መጥታ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ ጀነት እንድገባ ዱዓ አድርጉልኝ!!” ስትላቸው የእገሌ እናት ሆይ ጀነትኮ ባልቴቶች አይገቡም አሏት። ንግግራቸውን በግርድፉ ተረድታ ኖሮ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ከዚያ ሊነግሯት የፈለጉት ወደወጣትነት ተቀይራ እንደምትገባ እንደሆነ ሲነግሯት ተረጋጋች። የጀነት ሴቶችን የሚያወሳውን ቀጣዩን የቁርአን አንቀጽ አነበቡላት፡-

إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً فَجَعَلْنَاهُنَّ أَبْكَارًا عُرُبًا أَتْرَابًا

“እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው። ደናግሎችም አደረግናቸው። ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)።” (አል-ዋቂአ 56፤35-37)
ሀዲሱንም ቲርሚዝይና ሌሎችም ዘግበውታል።

አንድ ሰውም ግመል ላይ እንዲጭኑት ሲለምናቸው የግመል ግልገል ላይ እንጂ እንደማይጭኑት ነገሩት። “የአላህ መልእክተኛ ሆይ የግመል ግልገል ምን ይረባኛል!” ሲል ግራ በመጋባት ጠየቃቸው። እርሳቸውም “ማንኛዋም ግመል ከግልገል ውጪ ትወልዳለች!?” በማለት መለሱ። ይህን ሀዲስ ቲርሚዚይና አቡዳውድ አውርተውታል።

በመሠረቱ ሳቅና ጨዋታ እንደሚፈቀድ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላቱ የግድ ነው፡-

1. በውሸትና በመሠረተ ቢስ ፈጠራ ሰዎችን የምናስቅበት መንገድ መሆን የለበትም። እዚህ ላይ “ኤፕሪል ዘፉል” የተሰኘውን ከምእራብያውያን የተወረሰ ጨዋታን ማንሳት ተገቢ ነው። መሠረት የሌላቸው የቅጥፈት ወሬዎችን በማውራት የሚሠራ በመሆኑ ኢስላም ይቃወመዋል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

“ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ሰው ወየውለት! ወየውለት! ወየውለት! ወየውለት!!!” (አቡዳውድ፣ ነሳእይና ቲርሚዚይ ዘግበውታል።)
2. ሌላን ሰው የሚያንቋሽሽ ቀልድ መሆን የለበትም። የሰው ክብር ላይ ማላገጥ አይፈቀድም። ይህ የሚከለከለው ባለቤቱ ባልፈቀደ ጊዜ ነው። የሚሾፍበት ሰው ከፈቀደ ግን ችግር የለውም። አሏህ እንዲህ ብሏል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ። ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና። ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)። ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና። ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ። በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ።''

https://t.me/abu_abdurahman5
1.2K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 09:06:04 Join our Group using the following link

https://t.me/+STf8Cqtro56Tj3lV
1.1K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 20:29:40 Hey! Join our video chat: https://t.me/+STf8Cqtro56Tj3lV
1.3K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ