የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ “በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።” (አል-ፈጅር 89፤ 1-3) ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡- 《العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر》 “አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም ሰሂህ ሀዲስ ነው ብለውታል። ኢማም በይሀቂ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንደዘገቡት ደግሞ:- 《ليالٍ عشر، العشر الثماني، وعرفة، والنحر》 “አሥርቱ ሌሊቶች የመጀመሪያዎቹ ስምንቶቹ፣ የዐረፋ ቀን እና የእርድ ቀን ናቸው።” ብለዋል። https://t.me/abu_abdurahman5 589 views03:27