Get Mystery Box with random crypto!

እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግ | ሊቀ መዘምራን

እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡

ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡

የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡

ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS

Comment @Channel_admin09