Get Mystery Box with random crypto!

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/201 | ሊቀ መዘምራን

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•