ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። የትምህርት ቀን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ ለመጨረሻ ግዜ በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ዘ_ተዋህዶ_TUBE ለወዳጅ ዘመዶች SHARE ይድርጉ @Z_tewahido_tube 167 views06:16