Get Mystery Box with random crypto!

አንዲት ልጅ በINBOX መታ የሚከተለውኔ ጥያቄ ጠይቃኝ ነበር በአሁን ሰዓት ከ REFRENCE | AASTU Z-Campus

አንዲት ልጅ በINBOX መታ የሚከተለውኔ ጥያቄ ጠይቃኝ ነበር

በአሁን ሰዓት ከ REFRENCE ይልቅ TEXT BOOK ማነበብ ጠቃሚ ነው ትላለህ?

ምላሹ ለሌሎቻችሁም እንደሚያስፈልጋችሁ በመረዳቴ እንሆ ፦

REFRENCE BOOK ማንበብ አዋጭ ይመስላል አደል? አዋጭ ግን አይደለም ፤ ምክንያት

REFRENCE BOOKS ቁንፅል እውቀት  ያላቸው በመሆኑ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ አያረጋችሁም!

ከምትከተሉት REFRENCE ውጪ የወጡ ጥያቄዎች ቢኖሩ የመመለስ እድላችሁ ይቀንሳል ማለት ነው!

REFRENCE BOOKS የሚዘላቸው በጣም ብዙ ሃሳቦች እና ነጥቦች ይኖራሉ!

ከመጀመሪያው ሃሳብ ጋር እንዳይጣረስባችሁ በመጀመሪያው ሃሳብ ለማለት የፈለኩት ምንም እንኳን ሃሳቡ በሁለቱም መፅሃፎች  በ TEXT BOOK እንዲሁም REFRENCE BOOK ላይ ቢገኝም ፣ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ የመረዳት እድላችሁ የሚገኘው ከ TEXT BOOK ነው ማለቴ ነው!


በሁለተኛው ነጥብ ላይ እንድትረዱ የምፈልገው REFRENCE ሳያስተምሯችሁ ወይም ሳያነሱት የሚያልፉት ሃሳብ አለ!ስለዚህ አካሂዳችሁን መመርመር ያስፈልጋል!

REFRENCE BOOKS ላይ የሚጨመሩ የተነዛዙ ነገሮች ይበዛሉ!

TEXT BOOK ላይ የሌለ ነገር አምጥተው ፣ የመጨረሻ ሲቀባጥሩ ታገኟችሗላችሁ ፣ አንዳንዴ "እኔን ለማሳበድ ነው እንዴ ይሄ ሁሉ ነገር "ልትሉ ትችላላችሁ። የምመክራችሁ ነገር ከዚህ በፊት የወጡ የ ENTRANCE ፈተናዎችን በመቃኘት ፤ እድታነቡ ነው ። እንዲህ የተጨመሩ ነገሮች አንዳንዶቹ ለ ENTRANCE ጠቃሚ ናቸው ፣ አነሸዳንዶቹ ግን ጊዜያችሁን በከንቱ ነው የሚያቃጥሉት!

ትምህርት ሚኒስቴር የሚያውቀው አነብቡ ብሎ የሰጣችሁን TEXT BOOKS ነው!

አንዳንዶቻሁ ፈተናው ከ Extreme ወይ ከ Galaxy የሚወጣ እየመሰላችሁ ፤የተሰጣችሁ  Text book የትል እንዳለ እንኳን እረስታችሁታል!Guide ማንበብ የከፋ ነገር ባይኖረውም ፤ ማግኘት ከምትፈልጉት ውጤት በታች ለማግኘታችሁ ምክንያት ሊሆን ግን ይችላል!

600 በላይ ያመጡ ጓደኞቼን ጠይቄ ለማረጋገጥ የሞከርኩትም TEXT BOOK እንደሚያነቡ ነው!


ማሳሰቢያ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አንዳንድ ተማሪዎች REFRENCE BOOKS የስኬታቸው ሚስጢር እንደሆነ ሲናገሩም ይሰማል! ለአብነት ያክል ADVANCED ENGLISH BOOK ONE AND TWO እና EXTREME SAT ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው!


መልካም ዝግጅት ይሁንላችሁ

¢ ከቀሰም የተወሰደ !