Get Mystery Box with random crypto!

የአላህን(የፈጣሪን) ተዐምር መመልከት ከፈለግን የራሳችንን ህይወት መለስ ብለን እንቃኝ:: ብዙ አል | የኛ ለምን⁉️



የአላህን(የፈጣሪን) ተዐምር መመልከት ከፈለግን የራሳችንን ህይወት መለስ ብለን እንቃኝ:: ብዙ አልፈዋለው ያላልናቸው ቀናት የእድሜያችን አንድ አካል ሆነው አልፈዋል ... ምንም ያህል የከበደው ነገር ዛሬ ላይ እድሜ ቀላል ያደርገው ቢሆንም... :: አንችለውም ይከብደናል ብለን ፈርተን የሸሸናቸውን ጉዳዮች ሳይቀር በብቃት ተወጥተናል እንዴት ለሚለው ሁላ ምላሽ ላይኖረን ከመቻሉ ጋር...ታድያ እንደ እኔ እና አንተ ቢሆን ከፍርሃቱ ባልወጣን ያችም ከባድ ቀን ባላለፈች... ከዚህ በላይ ተዐምር ከየት ይገኛል??? ... እስካሁን ትላንታችን ላይ ያለው ባይገለጥልን እንኳን ዛሬ ላይ ብንፈልግ ተዐምር አናጣም ... እኛ ብቻ ለማየት ዝግጁ እንሁን!

(ጎበዝ, ዋጋው በወረደ ገንዘብ ይሄን የኑሮ ውድነት ችሎ መኖር መቻል ራሱ እኮ ተዐምር ነው )

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::