Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ለምን⁉️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yourstressfreezone — የኛ ለምን⁉️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yourstressfreezone — የኛ ለምን⁉️
የሰርጥ አድራሻ: @yourstressfreezone
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 352
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ ቤት ውስጥ ጭንቀት መድረሻውን ያጣል እናወራለን መፍትሄ እንሰጣለን ከስነፅሁፍም እንቃመሳለን መደጋገፉም አይቀርብን ተያይዘን ከስኬት ደጃፍ እንከትማለን ይግቡ...
@stressfreezonebot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-03 11:34:08


ሁሉም ሰው ራሱን ይወዳል የራሱን ጥቅምም ለማስከበር ይሯሯጣል፡፡ ይብዛም ይነስም ሁላችንም ውስጥ ያለ እውነት ይመስለኛል፡፡ አንዳንዶቻችን ላይ ግን ይህ ስሜት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከልክ ያለፈ ይሆንና ዙሪያችን ያሉ ሰዎች ላይ እንኳን ምን አይነት ነገር ሊፈጥር እንደሚችል ማሰብ ተስኖን ስለእኛ እና እኛ ብቻ እንኖራለን ሳይታወቀን ውስጣችን ይሻክራል በጊዜ ሂደት ምን እንዳደረኩት እንጃ ተቀይሮብኛል፣ ከሆነ ጊዜ ጀምራ ዘግታኛለች የሚል ስሜትን እናዳብራለን፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር እንኳን ራሳችንን ለመፈተሽ ሳይሆን ያንን ሰው ጥፋተኛ ለማድረግ ወደ ኋላ እንመለሳለን የሆነው ሆኖ ግንኙነቶች በዚህ ምክኒያት መቃቃር ይጀምራሉ መጨረሻውም ላለመለያየት የማለ የሚመስል የላይ የላይ ግንኙነት ይሆናል...ይሄን ሁሉ የዘባርቅኩት ራሳችንን ስንወድ በልክ እናድርግ ለማለት ነው።

መልካም ጁምዐ!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

202 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 08:27:42


የአላህን(የፈጣሪን) ተዐምር መመልከት ከፈለግን የራሳችንን ህይወት መለስ ብለን እንቃኝ:: ብዙ አልፈዋለው ያላልናቸው ቀናት የእድሜያችን አንድ አካል ሆነው አልፈዋል ... ምንም ያህል የከበደው ነገር ዛሬ ላይ እድሜ ቀላል ያደርገው ቢሆንም... :: አንችለውም ይከብደናል ብለን ፈርተን የሸሸናቸውን ጉዳዮች ሳይቀር በብቃት ተወጥተናል እንዴት ለሚለው ሁላ ምላሽ ላይኖረን ከመቻሉ ጋር...ታድያ እንደ እኔ እና አንተ ቢሆን ከፍርሃቱ ባልወጣን ያችም ከባድ ቀን ባላለፈች... ከዚህ በላይ ተዐምር ከየት ይገኛል??? ... እስካሁን ትላንታችን ላይ ያለው ባይገለጥልን እንኳን ዛሬ ላይ ብንፈልግ ተዐምር አናጣም ... እኛ ብቻ ለማየት ዝግጁ እንሁን!

(ጎበዝ, ዋጋው በወረደ ገንዘብ ይሄን የኑሮ ውድነት ችሎ መኖር መቻል ራሱ እኮ ተዐምር ነው )

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

210 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 16:01:40


ባማረ አለባበስ ውስጥ የደበቅነውን የተመሳቀለ አእምሮ ለማስተካከል ጥረት እስካልጀመርን ድረስ ውስጣችን ላይ ደስታን መፍጠር ይከብደናል ሁሌም ከምንኖረው በላይ ለሚታየው ማንነታችን ቦታ መስጠት እንጀምራለን ይሄኔ ነው ለሚያየን ኗሪ በውስጣችን ሟች መሆን ምንጀምረው

እናም አናስብበት


መልካም ጊዜ!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

193 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 09:49:50


ራሳችን ላይ ማተኮር ስንጀምር እኛ ዘንድ ያሉ ክፍተቶችን ማስተዋል ስለምንጀምር ስለ ሰው ጉድለቶች ምንጨነቅ እና ምናወራበት ጊዜም አይኖረንም ይልቁንም ራሳችንን የተሻለ ደረጃ በሚያደርስ ማንነት ግንባታ ላይ እንጠመዳለን:: ከፍታችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ደግሞ የሚያሳስቡንም ጉዳዮች በዛው ልክ የላቁ ይሆናሉ በተራ ጉዳዮች ላይ ጊዜን አናጠፋም እናም ምን ለማለት ነው ወደ ሰው ለመመልከት ምናጠፋውን ጊዜ ራሳችን ላይ invest በማድረግ አመርቂ ለውጥ በራሳችን ላይ እንፍጠር::

መልካም ውሎ ተመኘሁ!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

192 views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:55:16


ህይወት የምትሰጠን ፈተናዎች እምብዛም ከሩቅ የሚመጡ አይደሉም ከጉያችን እንጂ ... ጠላታችን እራሳችን ነን… ወይ ስንፍናችን አልያም ለሰዎች የሰጠነው ግምት ... ሁለቱም ለስኬታችን መሰናክል የሆኑ ፈተናዎቻችን ናቸው:: ቅርብ በመሆናቸው የሚዘነጉ ነገር ግን ደስታችንን ቀስ በቀስ እየሸረሸሩ የሚሄዱ ጉዳዮች ናቸው እና ልብ ብለን ልንሰራባቸው ግድ ይለናል::

የተዋበ ጁምዐ ተመኘሁ!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

4.5K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 15:18:11


ህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ነክራን ምርጫ ከማሳጣትዋ በፊት ያለንን ነፃ የሆኑ ጊዜዎች አስተውለን ለውሳኔ እንጠቀምባቸው:: በምናሳልፋቸው የትምህርት ጊዜያት ምን መማር እንደምንፈልግ መወሰን ካልቻልን ያለዕቅድ ባመጣነው ውጤት መሰረት የምንማረውን መንግስት አልያም ቤተሰብ ይወስንልናል... ተምረንም ስንጨርስ የተማርነው ከእኛ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆን አለመሆኑን በተማርንባቸው ዐመታት ላይ ለማሰብ ካልሞከርን ስንወጣ የተማርንበትን ሙያ ማስታወቂያ ቁጭ ብለን ስንጠብቅ ሌላ እድሜ እንፈጃለን:: ምን አይነት ባል ማግባት እንደምትፈልጊ ለራስሽ ቀድመሽ አስበሽ የማትኖሪ ከሆነ እድሜሽ ሄደ የመጣውን አግቢ ብለው ቤተሰቦችሽ ሲያስጨንቁሽ የመጣውን ወንድ ባል አድርገሽ መቀበል ግድ ይልሻል:: ህይወት አጭር ከመሆኗ ጋር የምትሰጠን አማራጮችም የጊዜ ገደብ ያለው ነው ምንም እንኳን የጊዜ ገደቡ እንደ ሁኔታዎቹ ቢለያይም የጊዜ ገደቡ ማለቂያ ላይ ለመወሰን ከመገደድ በፊት በነፃ አእምሮ በመወሰን የምንኖረውን ህይወት እንምረጥ...

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

199 viewsedited  12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 11:20:24


ወደ ስኬታችን ለመሰቀል መሰላላችን ላይ ከመውጣታችን በፊት ስለ መሰላላችን ጥንካሬ እና በትክክል መቆም እርግጠኛ እንሁን:: ምናልባት በትክክል ካልቆመና ጠንካራ ካልሆነ ዳግም እንዳንነሳ የሚያደርግ ስብራት ሊደርስብን ይችላል:: አንዳንዴ ጠንካራም ሆኖ በጥንቃቄ ለመውጣት ካልሞከርን አልያ ደግሞ ከአቅማችን በላይ ለመሰቀል ከሞከርን ስብራቱ ላይቀርልን ይችላል:: ስለዚህ በህይወታችን የምንሞክራቸው ሰበቦች እንዲው አደረስኩ ለማለት ሳይሆን የምር በማስተዋል መሆን አለባቸው:: ከልባችን ከቻሉ ካሰብንበት የማንደርስበት ምክንያት አይኖርም:: ካልሆነ ግን ጤነኛ ባልሆነ መሰላል ለመሰቀል ሞክሮ እንደመሰበር እንደመሰበር ይሆንብናል::

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

315 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 13:06:55


ሁሉንም ነገራችንን ለአላህ(ለፈጣሪ) እንደሰጠን ስናስብ ህይወታችን ላይ የሚገጥሙ መጥፎ አጋጣሚዎች እንኳን ሳይቀር በበጎ በመጠርጠር ምን አይነት ጥሩ ነገር ሊገጥመኝ ይሆን የሚል ስሜት ይፈጥርብናል:: የደረሱብን መሰናክሎች ለተሻሉ እድሎች እያመቻቹን እንደሆነ እናስባለን:: የችግሮቹን ውጥረት ለረጅም ስኬት መስፈንጠሪያ እንደሆነ በማሰብ አንማረርም:: አንዳንዴ ችግር ባይኖር ህይወት ጣዕሟ ምን ላይ ነው ያሰኛል ምክንያቱም በማጣት እና በመጨነቅ ውስጥ የነገሮች ዋጋ ማወቅ ስንችል አለፍ ሲል ደግሞ ከኢላሂ ጋር የሚኖረንን ግንኙነት እናጠብቅበታለንና...

መልካም ውሎ!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

310 viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 10:06:36


ከውጤቱ በላይ በሂደቱ መደሰት ከቻልን ሁሌም በአዲስ ተስፋ የመኖርን ሀይል እንጎናፀፋለን … ምክንያቱም ሙከራዎች ሁሉ ትርፋማ አይደሉም,ሁሉም ደግሞ አያከስሩንም::በዚህ ሁሉ የመሞከር ሂደት ውስጥ የህይወት ልምድ ይገኛል … በመታገል ውስጥ ደግሞ ተስፋ አለ … በትግል ላይ ሳለንም ከአላህ ተስፋ በማድረግ ውስጥ የምር ከአላህ ጋር ብቻ የመኖር ስሜት ይዋሃደናል:: ሰበብ ብቻውን ያለፍቃድ ዋጋቢስ ነውና ከፈቃጁ ጋር የመዋሀድን እድል ያጎናፅፈናል::ታድያ ከዚህ ውህደት የበለጠ ደስታ ምድር ላይ አለ???

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

6.6K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 12:09:07


ራሳችንን ምን ያህል እናምነዋለን?... በምናደርጋቸው ድርጊቶች, በህልሞቻችን ላይ የሚፈጠሩ አሉታዊ ተፅዕኖዎችንስ ምን ያህል የመቋቋም አቅም አለን?... ራሳችንን የማመን አቅማችንን እስካላሳደግን ድረስ ምንፈልጋቸውን ነገሮች እውን ለማድረግ እንቸገራለን:: ለእኛ የታየን እውነት እና የስኬት መንገድ ለሰዎች እንዲታያቸው ከጠበቅን መቼም የውስጣችንን አቅም የምናይበት መስመር መፍጠር አንችልም:: የህልም ጎዳናችንን ከመጀመራችን በፊት ራሳችን ላይ ያለንን እምነት እንትከል እንኮትኩት እናሳድግ ምክንያቱም የህልማችን ስር በራስ መተማመን ነውና...

መልካም ቀን!

@yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

294 views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ