Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yourpoim — ግጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yourpoim — ግጥም
የሰርጥ አድራሻ: @yourpoim
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.01K
የሰርጥ መግለጫ

Delighting your life is our job
👇
@bestpoim
For more
@pale_lighting

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 19:11:03 የትኛውን መጽሐፍ በPDF ይፈልጋሉ


ፍቅር እስከ መቃብር
▓⇨→READ
ዴርቶጋዳ
▓⇨→READ
ራማቶሓራ
▓⇨→READ
ክቡር ድንጋይ
▓⇨→READ
ኦሮማይ
▓⇨→READ
የአና ማስታወሻ
▓⇨→READ
ልጅነት
▓⇨→READ
ደራሲው
▓⇨→READ
አልኬሚስቱ
▓⇨→READ
ማህሌት
▓⇨→READ
አልወለደም
▓⇨→READ
አለመኖር
▓⇨→READ
ሌላ ሰው
▓⇨→READ
የሳጥናኤል ጎል
▓⇨→READ
አንድሮሜዳ
▓⇨→READ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
67 views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:41:40 እንዳላጣሽ (በድሉ ዋቅጅራ)
.
.
በመኖርሽ -
ማለዳ ወፎች ሲዘምሩ፣
ዜማቸው
ይገባኛል፤
በመኖርሽ -
ምሽት ጉጉት ሲያሟርት፣
ሰቀቀኑ
ያስፈራኛል፤
በመኖርሽ -
ጨረቃን አድማስ ላይ ሳያት፣
ውበት
ድምቀቷ
ያጓጓኛል፡፡

ብቻዬን
የለኝም ቅኝት፣
ብቻዬን
የለኝም ስስት፣
ብቻዬን
የለኝም ጉጉት፣

እንዳላጣሽ፡
389 viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:01:20
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

አንደገሃነም ቁልቁለት ፥
የፍም ድጥ የእሳት ኮረብታ
መጣሏን ባየሁበት ልክ ፥
ቃሌ ነፍስሽን አንሸራታ
በሲኦል ምሶሶ ቁመት ፥
በሀዘኔ ቁመት ከፍታ
ይቅርታ!

ክፋቴ ያላየችሁን ፥
ስላንቺ ከራስሽ በልጣ
ሳትገባ የያዘችዉን ፥
እሆድሽ ይዛ ብትወጣ
ባብተሸ ባነባሽዉ ልክ ፥
በዕንባሽ ቁልቁለት ስሞታ
ይቅርታ!

ለልመናሽ ጌታ ሆኜ ፥
አፈር ልሰሽ አንደምንጣፍ
አንደታቦት ተደግጌ ረግጬ ፥
ጠቅጥቄሽ ሳልፍ
ፊቴ ወድቀሽ አንደገና ፥
አፍረሻልና በኔ ፈንታ
እድሜ ባስቆጠረኝ ልክ ፥
የሐፍረት ሰጋር ትርታ
ይቅርታ!

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
መዘክር ግርማ
╰══•••┈ ወደመንገድ ሰዎች
┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈

አንድ ልጅ አዝማሪ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዘክር ግርማ በ አዲስ መጽሃፍ መጥቶልናል
ይነበብ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
422 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 07:34:19
@poemmylove
491 views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 07:31:09
ሳቅ እንዴት ይከብዳል?
.
.
ነፍስ አልባ ስብስብ
የራቀ ከመስህብ
ፍቅር የሌለበት ... የውሸት... የውሸት
እንዲህ ባለ ሳቅ ውስጥ የሞት ጥላ አለበት።
ይቀፋል ቀልዳቸው
ይጨንቃል ድምፃቸው
ሴትነትን ናፍቋል የሴት ተፈጥሯቸው።
አያምርም
አይደምቅም.. .
አንባርና አልቦው ...
ቀሚስና ጫማው.. .
በአባይ ፍቅር ነው ከወንድ የተቀማው።
ልብን አያሞቅም
ከብርድ አያስጥልም
ቃናቸው ይከብዳል
በእነርሱ ሽቶ.. . መዓዛሽ ይጣራል።
ከሎጋ ጣታቸው.. . ከእነሱ መዳበስ
ባንቺ ሻካራ ነው ... እኔ የምቀደስ ።
እንኳንም ሰማሁኝ
እንኳንም አዳመጥኩ
ከእነሱ ቁልምጫ.. . ባንቺ ጥሪ ወደቅኩ።
ጥሪው ሙሉ ስሜን ሲሻሽም አንተ በይ
እውነትሽ ደስ ይላል ... ስለማትታበይ.. .
የለም ደጅሽ ከቶ
ማስመሰል መሸንገል
ይሄ በቂዬ ነው ባንቺ ለመማለል ።
እንኳንም ኖርኩበት
ከንቱውን ኑባሬ
ይሄንን ግዛልኝ.. . ይሄንን አምጣልኝ
የሚል የቁስ ወሬ ...
በዝምታሽ ብቻ ተሰብሯል ቀንበሬ።
ስሄድ ነው ያወቅሁት.. . ስደርስ ደጃቸው
እንደምትበልጫቸው.. .
እንኳን አየኋቸው.. .
እንኳንም ቀረብኩኝ
በእነሱ ልኬት ዋጋሽን አወኩኝ
ከቀልድ ጨዋታቸው በኩርፊያሽ ማለልኩኝ
አሁን ተሸነፍኩኝ !
[ ሚካኤል አ. ]


•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጓድ ሚካኤል አስጨናቂ "ተቤራ" ከሚለው መጽሃፉ ቀጥሎ እነሆ "ሸግዬ ሸጊቱን" እንካችሁ ብሎናል ይነበብ !
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
471 viewsedited  04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 22:13:28 የራስሽ ውሽማ


የልጆች ዋጋ ውድ ነው ርካሽ
ሰልስትም አትቆይም ወረት እየነካሽ?

ፈውስ የለም
ዘላለም
ምን ሀኪም አስታሞን?
ሞትሽ የዘላለም ለቅሶሽ የአንድ የሰሞን::

እኔማ
ዕንባና ለቅሶሽን ወረትሽ አርሞት
እጠብቅሻለሁ
እስከምንግናኝ ደሞ በሌላ ሞት::

(እኛ እኮ ክፉ ነን)
ይኸውልማ
ሰው እንዴት ይሆናል የራሱ ውሽማ?
የሞቱ ውሽማ?
የነገው ውሽማ?

አንቺ የሰው ሲኦል አንቺ የሰው ገነት
ስንት ገባ ህይወት ስንት ነው ዜግነት?
ስንት ነው ሰውነት?
ስንት ነው ማንነት?

[ ኤልያስ ሽታኹን ]

•|••••••••••••••••••••••
Click here to Join
•|••••••••••••••••••••••
726 viewsedited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 13:52:03
@poemmylove
@poemmylove
@poemmylove
460 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 18:05:45
#ርዕስ_አልባ_ግጥም_2
.
.
በጠብ መንጃ አፈሙዝ የተገዛ ወንበር፣
በትውልድ ደም ላቦት የተገኘ መንበር።
.
.
አንከባሎ ያመጣው እስኪያጠፋው ድረስ፣
ሺ ቅልጥም ቢሰበር የሺ ሰው ደም ቢፈስ።
.
.
ለፌዝ እዘኑ እንጂ ከቶ አትሸበሩ፤
ወገን ገደል ይግባ!! ዝም ብላችሁ ምሩ፣
"ሀገር እግር ትብላ!!"
እስኪያቅረን ድረስ ቅዠቱን ደስኩሩ።
.
.
መቼም....
ቀን ያጣመመውን የትውልድ ደባ፣
ሲጎርፈው የኖረ የሻገተ እንባ።
በኪነጥበቡ እስኪያለሰልሰው፣
በ"ቢቸግር" ቅኝት ስቀን እናልቅሰው።
.
.
ዘመን ሲያባዝተው ቀን ሲያንቀው አክራሞት፣
ምንም ሆኖ ያልፋል የሰው ልጆች መሞት።!!

"........እንላቀስ ጎበዝ........"


ዓቢይ ( @abiye12 )

Join & share

@sinekal
@sinekal
@sinekal
467 views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 10:23:07 ናዕት

ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰአቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ...

... ቢጋረድ ሃሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እምአዕላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ህላዌ መሻት ዋዌው ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው

ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ" ...

ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ዘዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ

ከበሮ ግም ሲል በ እንቢ ነጓድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባ'ንት የልቤበ'ሳት

ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ እያለ ማሲንቆ

የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ
የጭብጨባው ጩሕት
እረጭ ሲል ውሸት
ይናገራል እውነት

የነፍስ ሕላዋ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው

ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ" ...

ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው...
ከሃገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም

ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላርለሳት
ቃል አለኝ እኔ ኖሬ ሞቼም ልክሳት ...


•••••••••••••••••
Click to Join
•••••••••••••••••
1.1K viewsedited  07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 15:51:25 #ርዕስ_አልባ_ግጥም
.
.
አንድም መሃል ኗሪ ቆላም ሁኑ ደጋ፣
ሚስጥራት ከታቢ ወይ ሁኑ ወሉ ጋ።
.
.
ብቻ................
የድሃ እንባ ያዘለ የደም ዶፍ እስኪጥል፣
ነፍሳት የቀጠፈ ህይወት እስኪቀጥል።
.
.
በአርምሞ ኑሩ እንጂ ምንም አትበሉ፣
ይልቅ ምድር ትልማ ችግኙን ትከሉ።


ዓቢይ ( @abiye12 )

Join & share

@sinekal
@sinekal
@sinekal
410 views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ