Get Mystery Box with random crypto!

ቢንያም ፀጋዬ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yopppp — ቢንያም ፀጋዬ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yopppp — ቢንያም ፀጋዬ
የሰርጥ አድራሻ: @yopppp
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 301
የሰርጥ መግለጫ

የተመረጡ የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ግጥሞች በድምፅ በፁሑፍ እንዲሁም በ pdf ወደናንተ በቻናላችን ይቀርባል።ለማንኛውም ጥያቄና አስተያዬት @Yop21

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-22 22:00:08 ስተውሸ

አንቺማ
:
ግዜ እንደ ሸክላ ፥ሰብሮ ንደጣለው
ንጉሰ የንግስና ፥ ዘውድ ንደሌለው
ገዢ ስልጣኑን፥ በትሩን እንዳጣው
የቀን ጎዶሎ ፥ የቀን ክፉ መቶ
መንግስት ባደባባይ ፥መለወጡን ወቶ
እንዳወጀው ብር፥እንዳሮጌው መቶ

ወድቄ ከግርሽ
ማሪኝ ብዬ ስለምንሽ
ግዜው አልፎብሃል፥
ብለሽኝ ተራመድሽ

#ግና.......

ከቶ አይጨበጥ ፥ተስፋዬ ጉም ሆኖ
ንፋስ እንደነካው፥ ደመና ተበትኖ
ራሴን ለውጬ፥ ስኖር ንደራሴ
ወቅቴን ጠብቄ ፥አብቤ ንደከሴ
ሃዘን ሳይዳብሰኝ ፥ሳይከደን ጥርሴ
ከዛ ከትርምስ ከሰው ግርግር
ሾልኮ ንደወደቀ ፥እንዳዲሱ መቶ ብር
ጎንበስ ብለሽ አንስተሽኝ
እኔ ግን የሰው ነኝ
አንቺ አገኘሁ አልሽኝ።


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
181 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 21:58:17 ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ለቀናት በተለያዩ ምክንያት ከናንተ ርቄ ብቆይም እንሆ አሁን ተመልሻለሁ።
አብራችሁኝ ስለሆናችሁ በፈጣሪ ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
152 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, edited  18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 11:44:09 "ዘተጠመቀ ወዮርዳኖስ "

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

@YOPPPP
214 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 23:08:43 የትግስቴ ዳሩ

እንግዳ ሳለ፥ እምቦሳው ለምድር
መቆም ተስኖት፥ አስደግፈው ማገር
እትብቱ ሳይደርቅ፥ ሳይቆርጡለት ጥፍር
እናቲቱን አልበው ፥ አደረጉኝ እንገር

ያሁን እኔን ፥ጥሬ ብለው
ነገን ሳይሆን፥ ዛሬን አይተው
በያ ከሴ፥ ቅል አጥነው
ሰላም ያለው፥ ነጩ ህይወቴ
ጥሬ ሲሉት ፥ረግቶ ቤቴ
ቅላቸው አኑረው ርጎውን ማንነቴ
ሲገፉኝ ................ስገፋ
ስገፉ....................ስገፋ

ገፊዬን ስያልበው፥ ሆኜ ሀሞተ ኮስታራ
ዝምታዬ ቅቤ፥ ትግስቴ አሬራ
ምላሼን ገፊዬ፥ ንጦ ተኩራራ

ደሞ መች አሸ፥ ከሴራው መቆጠብ
በሀሳብ ብዕር ፥ለንደገና በደል ሲተይብ ሲተይብ
እፍሙ ላይ ጥዶ፥ አደረገኝ አይብ

ከንግዲ ወድያ በቃኝ፥ ሆኛለውኝ አጓት
ወይ ጠጣ ወይ ድፋኝ፥ ልክም አለው ትዕግስት


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
239 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 16:19:21 እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኃል

ሉቃ 2፥11

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


@YOPPPP
228 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, edited  13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 23:10:56 ያሰው

ካንድ ጥግ ፥ካንድ ቦታ
ያቺ አበባ ፥ ላይን ሞልታ
ልብ ምሰርቅ ፥ ሁና ታይታ
እንቡጧ ሲፈነዳ
ስፈካ ፅገሬዳ
በቁንጅና ልቡን ንዳ
ለቅንጠሳ በስሜት የተነዳ
እሷን ለራስ የዳዳ የዳዳ
ዘዴ ዘይዶ ለሾኳ ብልሃት
ተራቆ ረቆ ልቆ ቀንጥሷት
በጥበብ ለስልሶ ምጓት ምጓት
ስጠወልግ እንደ ጉዝጓዝ ረገጣት።


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
264 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 12:41:30
ይህ ወቅት ልዩነቶቻችንን ለአፍታም ቢሆን ሸሸት አድርገን በአንድ የምንሰለፍበት ጊዜ ነው። በመጎሻሸም ድል አይመጣም። በመወቃቀስ ድል አይገኝም። ለመተቻቸት፣ ለመወነጃጀል መቆምያ ያስፈልጋል። የምንቆመውም የምንኖረውም በኢትዮጵያ ነው። ሃገር ህልውናዋን እያጣች ጣት መጠቋቆም መወቃቀስ ምንድነው? ከሁሉ በፊት ሃገር ትቁም!

አድዋ ላይ ነጭን ድል ያደረግነው የውስጥ ሽኩቻዎች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። በየቦታው የርስ በርስ ግጭቶች ነበሩ። የጋራ ጠላት ሲመጣ ግን ሁሉን ትተው በአንድ ቆሙ። በአንድነት ድል ነሱ! እስከዛሬ ድረስ አድዋ እያልን የምንኮራበትን፣ በነጭ ፊት የምናቀረቅርበትን ሳይሆን በክብር ቀና የምንልበትን የድል ቀን ጽፈውልን አለፉ።

ታሪክ ራሱን ይደግማል!

ከየቦታው ጦር ወደኛ እየተሰበቀ ነው። እንዴት ነው ይህን ጦር ልንጋፈጠው የምንችለው? እንዴት ነው ኢትዮጵያን እንድትቆምና የአርብ ስቃይዋን በትንሳኤዋ ልናፈካው የምንችለው? በመወቃቀስ? ጣት በመጠቋቆም? በፌዝ?

ሁሉም ልክ የሆነ ጊዜ አለው። ሁሉም በጊዜው ይጠየቅበታል። ከሁሉ በፊት ግን የሃገር ህልውና ይቀድማል!

ወደሞት እየሄድክ ስለውርስ፣ ስለገንዘብ አታነሳም። እግርህ እየተቆረጠ ስለጫማ አታስብም። ጫማ ለማድረግ እግርህ እንዳይጎዳ ከእንቅፋቶች መከላከል አለብህ! ወደድክም ጠላህም ያለሃገር መቆምያም መኖርያም የለህም!

በአንድ ሆነው መኖርያ ሃገራችንን፣ የክብር ጌጣችንን፣ ኢትዮጵያችንን ሊያጠፏት ሲመጡ በአንድ ሆነን እንመክታቸው። በመጎሻሸም ድል አይመጣም። በመወቃቀስ ድል አይገኝም።

እኛ ያለ ኢትዮጵያ ምንም ነን። ሁሉ ነገራችን የተሰፋው፣ ማንነታችንን የተሳሰረው ከኢትዮጵያ ጋር ነው። ስንቱን የጊዜ ማዕበል ተሻግራ መጥታ እኛ ጋር ስትደርስ አትፈርስም!

እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን!


መላኩ ደምሴ!
264 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-08 23:01:06 መንጋው ሳይንጫጫ!!


ሳትኖር ኑራ፥ ሸሽጋ በናት ጉያ
ሁሉን በአንድ ፥ ታቅፋ ዙሪያ
ወጨፎ ውሽንፍሩን፥ ሁና መዝጊያ
ሳትበገር፥ ከሌት ቁፍኝ አሳድራ
ጥሬን ሲሹ ፥ ዳዋን ጭራ
ራስ ደፍታ በሁለት እግር
ለልጆቿ ስትታትር
በጥበቃ ኮሲን ስጭር

#ግና

ለጋ እንጭጭ ፥ በቄጤማ ጉልበት
ድሃ ተሰውራ ፥ መንጋ ሆነው ከሚሄዱት
ከናት እይታ ፥ ገሸሽ ያለች ጫጩት
ሲሳይ ሆነች ፥ ለጩሉሌ ለጭልፊት።


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
220 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-08 23:01:06 ጥላዬ

ገፄን መሬት ላይ ፥ ስሎ ብርሃኔ
አብሮኝ የተጓዘ ፥ ሳይታክት በቀኔ
እንደ ደጀን መከታ ፥ አሌኝታ ከጎኔ
ላፍታ ሳይለይ ፥ አንዳች ሳርቅ ካይኔ
እንድ ራሴ ተስሎ ፥ መላ አካላቴ
እንደ ጅራት ከዋላ ፥ እንደ ቀንድ ከፊቴ
ስሄድ ሲከተል ፥ በኔ ፋና ኮቴ
ጀምበር ስጠልቅ ቀኔ ሲመሽ፥
ምነው ጠፋህ ጥላሞቴ


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
208 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-08 23:01:06 ለምን?

ሀገሬ እንደ ቆንጆ ሴት ፥ ፈላጊዋ ብዙ
ተፈጥሮ ፀጋን ችራት፥ ቀልብን ሚገዙ
ለፅኑ አፍቃሪዋ ፥እልፍ ሆነ መዘዙ

ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP
173 viewsቢንያም ፀጋዬ 21, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ