Get Mystery Box with random crypto!

አንቺን ብዬ! ያኔ ማፍቀር ስም አሰጥቶኝ እኔን እኔ ሳልሆን ብዙ አሳይቶኝ | ቢንያም ፀጋዬ

አንቺን ብዬ!

ያኔ ማፍቀር ስም አሰጥቶኝ
እኔን እኔ ሳልሆን ብዙ አሳይቶኝ
እልፍ አስደንብሮኝ
ለፍቅር፥ስገዛ እንደ ባሪያ ወዳሻሽ ወስደሽኝ

በብልጠት ልጓምሽ፥
ከጀርባዬ ላይ ኮርቻሽን ጭነሽ
በለበቅ አለንጋ ፥
ሽምጥ እንድፈረጥ መውደዴን አስታከሽ
ቼ ቼ ቼ እያልሽ ስጋልቢኝ፥
ፈርጥጬ አድርሼሽ

ሳታወልቂ ልጓም ፥ሳትፈቺ ኮርቻ
ምን ይሉታል እኔን ከጥግ አስሮ፥ ከሌላ ጋብቻ

ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP