Get Mystery Box with random crypto!

አንባቢ ሆይ 'ጸጋ' ምንድ ነው? 'ጸጋ' እግዚአብሔር ለሰዎች የሳየው ፍቅር እና ምህረት ነው። | የመስቀሉ ፍቅር ✞

አንባቢ ሆይ "ጸጋ" ምንድ ነው?

"ጸጋ" እግዚአብሔር ለሰዎች የሳየው ፍቅር እና ምህረት ነው። "ጸጋ" መለት እንዲው የሆነ "ነጻ ስጦታ" ማለት ሲሆነ ፤ ይህም ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ ነጻ ስጦታ ነው። እግዚአብሔር ጸገን ለሰዎች በነጻ(እንዲው) ሰጠ። ሰዎች ኀጢአተኛ ሰለሆኑ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ምህረት ለመቀበል አይችሉም። ነገር ገን ምንም እንኳን ሰው የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማግኘት የማይገባው ቢሆንም ከእግዚአብሔር ፍቅር እና የርህራሄ ልብ የተነሳ ፣ ይህ የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች የተገባ ሆኗል። እኛ ኀጢአተኞች እና የእግዚአብሔር ጥላቶች ሆነን ሳለን እግዚአብሔር የገዛ ልጁን እንዲያድነን ወደ እኛ ላከው ፣ በገዛ ልጁም ከሞታ እና ከኃጢአት ባረነት አዳነን። (ሮሜ 5፥8) (ዮሐ 3፥16)።

ከዚህም የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ደህንነታችንን አጊንተናል። (ኤፌ 2፥8 ፤ ቲቶ 2፥11)። ደህንነት የሚገኘው በጸጋ ነው። መጽሐፍም እንደሚል “ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” — ኤፌ 2፥9 ፤ ለማይገባው የሰው ልጅ እንዲገባ ከተገለጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ። ከዚህ ውድ ጸጋ የተነሳም የክርስትናን ህይወት እንኖራለን። የሰው ልጅ የገኘው መንፈሳዊም ሆነ ቁሳዊ በረከቶች ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልጁን ላከልን ፤ ቅዱሳንም ሊየረገን በጸጋው መንፈስ ቅዱስን ላከልን። ከዚም ለሰዎች ከተ ገለጠው ከተትረፈረፍው ጸጋም የተነሳ በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ።

ተባረኩ ከታናሻቹ...!!!