Get Mystery Box with random crypto!

#SD_(Secure Digital)_Card #ሜሞሪ_ካርድ × ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራች | Yidnek Tube

#SD_(Secure Digital)_Card
#ሜሞሪ_ካርድ

× ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ 'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤተሰቦች!

× የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ ሜሞሪ ካርድ ወይም SD (Secure Digital) CARD በጥቂቱ እነግራችኃለሁ አብራችሁኝ ቆዩ!

× ይህች SD (Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡

× ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮምፒዩተሮች፣ በታብሌቶች፣ በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

× የሜሞሪ ካርድ በመጀመሪያ ወደ ዓለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡

× እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሜሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሜሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

× በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሜሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በኢንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡

× አብዛሃኞቹ ሜሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

× ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሜሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ፡፡

× በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡

× ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

× በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሜሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡

× Compact Flash የተባለው የሜሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡

× እነዚህ የሜሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

× እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሜሞሪ ስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር፡፡

× በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ SD CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

× አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm (mili meter) ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1TB (Tera Byte) ወይም 1000GB (Giga Byte) መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡

× ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሜሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB (Mega Byte) ነበር፡፡

× ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡

× ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-

- 16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
- 7500 ሙዚቃዎችን
- 3200 ፎቶዎችን
- ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube