Get Mystery Box with random crypto!

• ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤቴሰቦች! • | Yidnek Tube

• ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤቴሰቦች! •

× ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አምስት ነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ዌብሳይቶችን እጠቁማችኋለሁ፤ እብራችሁኝ ቆዩ!


፩ኛ. MIT Open እና Courseware

- የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረ-ገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኦንላይን ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው።

- ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

- ሊንክ፦ https://alison.com/certificate-courses?utm_source=google&utm_medium=cpc&utm_campaign=PPC>Tier-3>Product>Courses-(Broad)&gclid=Cj0KCQiAh4j-BRCsARIsAGeV12CcIrBDHwNbJVmkObIuPKFRh2NpNq03_SzlOZILG8xkijzKN9gYBIMaAlQJEALw_wcB


፪ኛ. GitHub.com

- GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድረ-ገጽ ነው።

- እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድረ-ገጽ ዓይነት ነው።

- ሊንክ፦ https://github.com/


፫ኛ. W3 Schools

- ይህ ድረ-ገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፣ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ ፕሮግራሚን ቋንቋዎች የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።

- በተጨማሪም በድረ-ገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

- ሊንክ፦ https://www.w3schools.com/


፬ኛ. Codecademy

- አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድረ-ገጽ ነው።

- በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።

- ሊንክ፦ https://www.codecademy.com/


፭ኛ. Stanford Engineering Everywhere (SEE)

- ይህ ድረ-ገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው።

- ድረ-ገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም፦ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

ሊንክ፦ https://see.stanford.edu/


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube