Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━── | ይሁዳ የጥበብ ልጅ ፩

​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──


አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል። ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ። ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል። ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል። በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ። ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ። ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው "ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ?ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?" ብሎ አምባረቀበት። አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት "ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ። ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል" አለው። ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።

በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው። ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆም ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን። የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል። በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን። ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችን እንብሰለሰላለን እንጎዳለን። መፍትሄው ምንድን ነው?

• ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።

• ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።

• ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር። በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
Only

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌🇯 🇴 🇮 🇳

ባለቅኔው

https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb

#ለመቀላቀል ይጫኑ

#ለተጨማሪም_አስተያየቶ_እና_ልምዶን_ለማካፈል @Yehudaw ☜