Get Mystery Box with random crypto!

የዘመን መጨረሻ! ክፍል~ሰባት እስራኤልን በአስራ አንደኛው ሰዕት በጉ በአርማጌዶ ምድር ነገስታቶ | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

የዘመን መጨረሻ!
ክፍል~ሰባት

እስራኤልን በአስራ አንደኛው ሰዕት በጉ በአርማጌዶ ምድር ነገስታቶቹን ድል ሊነሳ ይደርስላታል።ይሄ የሆነበት ምክንያት ነገስታቶቹ በእስራኤል ላይ በጣም ሲበረቱባቸው፥ በዛም ምክንያት እስራኤላውያን ኪዳን ወዳላቸው አምላክ ቀና ይላሉ።በዛን ሰዕት በህይወት የሚተርፉትም ሁሉም እስራኤላውያን ይድናሉ።ኪዳን ኢየሱስነው። በዛን ጊዜ ሁሉም ያዩታል።ሲመጣም አማኞችን ሊነጥቅ እንደመጣው እስከደመና ድረስ ሳይሆን እስከ ምድር ድረስ ይመጣል።የሚመጣው አንድም ነገስታትን ድል ሊያደርግ፣ ለእስራኤል የገባውን ኪዳን ሊፈጽምና በምድር ለአንድ ሺህ አመት ብቻ የሚመሰረተው የእግዚአብሔርን መንግስት ለመመስረት ነው።አርማጌዶ ላይ የሚደረገው ውግያ በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የተለየ ነው።ፍጡር አምላኩንና ጭፍራዎቹን ሊወጉ የሚሰለፉበት ጦር።ነገስታትም በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።ራእይ 19፥19

ዮሐንስ በራእይ ያየውን ተመልከቱ።ምስራቃውያንና ሌሎች የዓለም ነገስታት፣ በአውሬው፣ በሐሰተኛው ክርስቶስና በሐሰተኛው ነቢይ ጋር በመሆን ከሰማይ የሚገለጠውን ንጉስና አብረው የሚመጡትን አማኞችን ለመውጋት ይከማቻሉ።አሁን የምታዩትን መሳሪያ ያን ጊዜ ሊጠቀሙበት አርማጌዶ ላይ ይሰበሱቡታል።ሲያስቁ።ኢየሱስ እፍፍ ቢል እንደሚተኑ አላወቁም።የሚገርመው መጽሐፍ ሲናገር ይጨፈልቃችዋል ነው የሚለው።ነገስታት የሚያግዛቸው ብዙ ነገር አለ፤ በጉ ኢየሱስ ግን ብቻውን ይረግጣችዋል።በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።ራእይ 19፥13 በደም የተረጨው ልብስ፥ እርሱን ለመውጋት የሚሰለፉትን ነገስታት እንደሚጨፈልቃቸውና በምድርም ታይቶ የማይታወቅ ደም እንደሚፈስ ለማሳየት ነው።

አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፦ መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።ራእይ 19፥17-18 አንበሳውን ሊወጉ የተዘጋጁ ነገስታት በበጉ ድል አድራጊት ይጠናቀቃል።በሰባት ወር ተሰብስቦ የማያል የሰው ልጅ ሬሳ በዛ ምድር የሚበዛበት ጊዜ፣ ደም ጎርፍ እስኪመስል በምድር የሚጨቀይበት ጊዜ ይሆናል።በነጭ ፈረስ ላይ የነበረውም ልብሱ በደም የተረጨ ነበር ይላል ቃሉ።ኦ ጌታ ሆይ! ከዚህ ቁጣ ስለሰወርከንና በቁጣው ሰዕት አብረንህ በከበረ ማንነት ስለምንገለጥ እናመሰግንሃለን።ሙሽሪት የሙሽራዋን ድል አድራጊነት በአካል አብራው የምትመለከትበት ወቅት ነው።ሃሌ ሉያ!አሜን።

አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።ራእይ 19፥20-21 እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን በዛን ሰዕት ጌታ ኢየሱስ ድል የሚነሳቸው የሚጨፈልቃቸው በዛ ጦር ላይ የተሳተፉትን ነገስታትና አውሬውን ነው።የተቀሩትን አይነካም።በዛ ጦር ያልተሳተፉ አሕዛቦችና እስራኤላውያንን አይነካም።በምዕራፍ ስድስት ላይ በሱባኤው አጋማሽ ላይ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉት ሁሉ ከአውሬውና ከሐሰተኛው ነቢይ ጋር ወደ ጥልቅ ይጣላሉ።ሐሰተኛው ክርስቶስም ወደ እሳት ይጣላል።በዛን ቀን ማንም በበጉ ፊት የሚቆም አይኖርም።ምክንያቱም ኢየሱስ ያን ጊዜ ወደምድር የሚመጣው እንደሚታረድ በግ ሁኖ ሳይሆን እንደሚያገሳ አንበሳ ነው።

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet