Get Mystery Box with random crypto!

.እና እንደፈራሁት... ከመገኘት ቀድሞ ንጥል የበዛ እንደው ፣ መስከኑ ተሽሮ ድፍርስ ጣ'ም ከሆነ | የጥበብ ቤት

.እና እንደፈራሁት...
ከመገኘት ቀድሞ
ንጥል የበዛ እንደው ፣
መስከኑ ተሽሮ ድፍርስ ጣ'ም ከሆነው ፣
ነገ ትርጉም ያጣል፤
የሰጡትን ንቆ የራሱን ይፈጥራል።
ድፍርሱም ሲመረው ትላንትን ይደግማል።

ልክ እንደሚያስፈራው...
የሰዓት እላፊ ነጎድጓዳ ዝናብ
የኔ እና ያንተም ነገር
ልቡ ርዷል መሰል ማስገምገም ጀምሯል።
ውዴ...!
ያስፈራል ሂደቱ
አኳኋን ሁነቱ
ሰቅዞ የያዘን የነፍስ አለም ፍቅር
መናፈቁ ቀርቶ አይሏል ቁጭቱ።
ያስፈራል...!
ያስፈራል ሂደቱ
ምን ብዬ ልጀግን ሁሉም ላንተ አብረው
ሲያገሉኝ ቀናቱ!?
ብቻ ይሄም ያስፈራል...
የህይወት ሁነቱ!!

ፊያሜታ

@YETBEB_BET