Get Mystery Box with random crypto!

በረመዳን ምን ይጠበቅብናል? (ክፍል 2) የምህረት ወር የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- | °♡•የረሱል ኡማ°♡•

በረመዳን ምን ይጠበቅብናል? (ክፍል 2)

የምህረት ወር

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-

رغم أنف رجل دخل عليه رمضان ثم انسلخ قبل أن يغفر له

“ረመዳን ገብቶ ከዚያም ምህረት ሳያገኝ የወጣበት ሰው አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ያግኘው)!”

በረመዳን ምህረትን ያላገኘ መቼ ያገኘዋል እንበል?…

ከአኼራ ርቆ የዱንያ ባህር ውስጥ እየዋኘ ምህረት ሊያገኝ?… የብርና የወርቅ ኮቴን እየላሰ… በልጆችና በሚስት ፍላጎት እየተነዳ ምህረት ሊቸር?…

በእርግጥ እኛ ማንንም ከአላህ ምህረት ተስፋ አናስቆርጥም። ነገር ግን አላህ እንደነገረን ምህረት ሠበቦች አሉት። ጀነት ለመግባት መስፈርቶች አሉ። ኢማን በምኞት አይደለም። ልብ ውስጥ የዘለቀ እና በተግባር የተረጋገጠ ካልሆነ። የምንለው እውነት ነው!  ከፈለጋችሁ ይህን አንቀፅ አስተውሉት። እንዲህ ይላል፡-

وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ * الَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ * وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ * أُولَٰئِكَ جَزَاؤُهُم مَّغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ

“ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩየተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ። ለእነዚያ በድሎትም ኾነበችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችምይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)። አላህም በጎሠሪዎችን ይወዳል። ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህንየሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድምየለ። (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)። እነዚያምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸውዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውገነቶችም ናቸው። የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛአማረች!።” (አሊ ዒምራን 3፤ 133-136)

ለጀነት የተዘጋጀ ይኖር?!

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለው ጠየቁ፡-

“ለጀነት የተዘጋጀ ሰው አለ?! ጀነት ልብ ውስጥ ትዝ ብላ የምታውቅ አይደለችም። በካዕባ ጌታ እምላለሁአንፀባራቂ ብርሀን ናት! የሚንቀጠቀጥ ደስታ ያላት፣ብርቱ ህንፃዎች ያሉባት፣ ሰፋፊ ጅረቶች ያሉባት፣ ብስልፍራፍሬዎች የሞሉባት፣ ያማሩ ሚስቶች ያሉባት፣ ብዙሙሉ ልብሶች የሚገኙባት፣ ዘላለም የሚኖርባት፣ ሰላምየሠፈነባት፣ ባማሩ አረንጓዴ አትክልቶች የተሸፈነች፣በታላቅ ደስታና አስገራሚ ፀጋዎች የተሞላች ሀገር ናት።”

ጀነት መግባት- ከአላህ ከሚከጀል እዝነት በተጨማሪ- ብዙ ድካም ይጠይቃል። አላህን ለመታዘዝ የምንከፍለውን መስዋእትነት ይፈልጋል። አዎን! በዚህች ዱንያ ውስጥ የምንቆየው ጊዜ አጭር ነው። ከዚያም ረዥም አመታት ይከተላሉ። መጨረሻ የላቸውም። ቀብር ከዚያም የምፅአት ሀገር…. በዚህች አጭር የዱንያ ህይወት ውስጥ ተዘናግተው ያለፉ ሰዎች ከአላህ ጋር ሂሳብ ለማድረግ በሚቆሙ ጊዜ ልባቸውን የሚሞላው ቁጭት ምን ያህል ከባድ ይሆን!? ከጌታቸው መብት ያጓደሉ ባሮች አስፈሪው ሚዛን ላይ ሲቆሙ የሚሰማቸው ብስጭትስ ምን ያህል የከፋ ይሆን?! እስቲ እነዚህን አንቀፆች እናስተውል፡-

قَالَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِي الْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ * قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَاسْأَلِ الْعَادِّينَ * قَالَ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا ۖ لَّوْ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ * أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

“በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትን ቆያችሁ?”ይላቸዋል። “አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን። ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ ” ይላሉ። “እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ  ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ በምትቆዩት አንፃር)  ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም” ይላቸዋል።  “የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ  መኾናችሁን ጠረጠራችሁን?” (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)”  (አል-ሙእሚኑን 23፤ 112-115)

የቀብር ሰዎች ውድ ምኞት ለአፍታም ቢሆን ወደ ዱንያ መመለስ ነው። አንድ ጊዜ ወደ ህይወት ተመልሶ አላህን ማወደስ፣ ሱብሀነሏህ ማለት፣ አንዲት ጊዜም ቢሆን ለአላህ መስገድ…

እኛስ ከነርሱ አንማርም!? አሁንም ከእንቅልፋችን አንነቃም?! የሚጠብቀንን ፍጥጫ ለመጋፈጥ አንዘጋጅም!? አሁን ዱንያ ውስጥ ፊታችን ላይ የቆሙ ለመጪው አለም የምንሰነቅባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። ይኸው ረመዳን ወዲህ እየጠራን ነው። እስኪ እጅጌያችንን አጠፍ አድርገን፣ ፍራሻችንን ትተን፣ ቤተሰቦቻችንን አንቅተን፣ በነፍሳችንና በስሜታችን ላይ የጂሀድ ባንዲራ አንግበን እንነሳ!!

ኑ የአላህን ጥሪ አሺ እንበል!

اسْتَجِيبُوا لِرَبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُ مِنَ اللَّهِ ۚ مَا لَكُم مِّن مَّلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٍ

“ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱበፊት ለጌታችሁ ታዘዙ። በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም።  ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም።” (አሽ-ሹራ 42፤47)

ሠዎችና ረመዳን

አዎን! ረመዳን በአመት አንዴ ብቻ የሚከሰት ታላቅ እድል ነው። ነገር ግን ሙስሊሞች በዚህ መልኩ ይተዳደሩት ይሆን? አንዳንዶች የዚህን ወር መምጣት እንደ ከባድ ሸክም ይመለከቱታል። ቶሎ እንዲያልቅም ይመኛሉ። እነዚህ ከረመዳን የሚያተርፉት ከረህመት መባረር ብቻ ነው። ረመዳን ገብቶ ወጣ እንጂ በህይወታቸው ላይ የሚጥለው መልካም አሻራ የለም። አንዳንዶች ደግሞ የረመዳንን ዋጋ ተረድተዋል። እንዲህ አይነቱ ሰው የበረታ ክንዱን አዘጋጅቷል። የቻለውን የአምልኮ ተግባር ለመፈፀም መንፈሱ ነቅቷል። ልቡ አብሮት ባይኖርም ብዙ ጊዜ ቁርአን ለማኽተም፣ ብዙ ለመስገድ፣ ብዙ ዒባዳዎችን ለመሥራት አቅዷል። ይህ አይነቱ ሰው መዳረሻ የነበሩትን የአምልኮ ተግባራት ግብ አድርጎ ይዟቸዋል። ፆም ሊያረጋግጠው የመጣለትን ትልቁን አላማ ግን ዘንግቷል። በእርግጥ ረመዳን በእነዚህኞቹ ልብ ላይ ጥሩ ስሜት ጥሎባቸው ያልፍ ይሆናል። ግን ረመዳን እንደወጣ ቀናት እንዳለፉ ወኔያቸው አብሮ ይከስማል።

አንዳንዶች ደግሞ ረመዳንን ቀልብን ህያው ለማድረግ፣ ከእንቅልፉ ለማንቃትና በውስጡ ላይ የተቅዋን ችቦ ለማቀጣጠልና የኢማንን ሥር ለመትከል ምርጥ አጋጣሚ አድርገው ያዙት። እነዚህኞ