Get Mystery Box with random crypto!

የቁርአን ቤተሰቦች

የቴሌግራም ቻናል አርማ yequranbeteseboch — የቁርአን ቤተሰቦች
የቴሌግራም ቻናል አርማ yequranbeteseboch — የቁርአን ቤተሰቦች
የሰርጥ አድራሻ: @yequranbeteseboch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 726
የሰርጥ መግለጫ

😍ቁርዓን😍
የቀልብ መድሀኒት ፣ የህይወት መመሪያ ነው

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 13:37:16 ሰላት ዐለ ነቢ ﷺ ያበዛ አላህ ልቡን ብርሀን ያላብሰዋል ..

ምክንያቱም ወንጀሎች ልብን ያጠቁራሉ ፤ አንድ ባርያ ወንጀል ሰራ ልቡ ላይ ጥቁር ነጥብ ይነጠብበታል ፤ በዛም ወንጀል ከቀጠለና ከተጨማለቀ ያቺ ጥቁር ነጥብ ሰፍታ ልብ ሙሉ ጥቁር ጨለማ ይሆናል...

አላህ ምላሱን በሰላት ዐለ ነቢ ﷺ ሲያረጥበው ደግሞ ወንጀሉ ተራራን ቢያክል እንኳን ይማራል ፤ ወንጀሉ ሲማር የልቡ ጥቁረት እየጠፋ ይመጣና ብርሀን ይፈነጥቅበታል "


- ኢብኑል ጀውዚይ / ቡስታኑል ዋዒዚን (289)

@yequranbeteseboch

Join it Share it
105 views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:39:00 ሰውዬው ሌት ተ ቀን ዒባዳ እያደረገ ከጌታው ጋር ቅርበት ለመፍጠር ይጥራል።
ከእለታት አንድ ቀን በሌሊት ተነስቶ ጌታውን ሲማፀን ኢብሊስ ይመጣ ና እንዲህ
ሲል ሹክ ይለዋል፦‹‹እስከመቼ ነው አላህን ስትማፀን ከርመህ አንዲትም ምላሽ
እማይመጣልህ? መቼ ነው ያንተ ዱዓህ ተቀባይነት አግኝቶ ውጥንህ
ሚሰምረው?››
ባርያ ቅስሙ ተሰበረ፣ ሀሞቱ ፈሰሰ፣ ሞራሉ ተነካ፣ ከአምልኮውም ተዘናግቶ
በብስጭት ጥላ ስር ተጠለለ።
ከእለታት አንድ ሌሊት በእንቅልፍ ተውጦ ሳለ የህልም ተጣሪ እንዲህ ሲልም
ተጣራ፦‹‹ባርያ ሆይ! ስለምን ከአምልኮ ተቋረጥክ? ስለመቋረጥህ ምክንያት
ይኖርህ?! ››
ባርያውም በህልም ሰመመን እየዋለለ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፦‹‹አላህ
ተማፅኖዬን አልሰማህ አለኝ፤ ምናልባትም እኔ ከደጃፉ የተባረርኩ እና የተጠላሁ
መስሎ ታየኝ፤ ጠፋሁም››
ተጣሪውም እንዲህ ሲል ምላሽ ይሰጠው ጀመር፦‹‹በፍፁም ከደጃፉ
አልተባረርክም። አላህን ማወደስህ እና መማፅንህ አላህ ዘንድ ተፈላጊነትህን
እና ቅቡልነትህን ማመላከቻ ነው። ያ ባይሆንማ ምትሻውን ሰጥቶ ከደጃፉ
ባባረረህ!
አላህም እንዲህ ይልኃል "እኔ ነኝ እኮ ወደ እኔ መዋደቅን እና እኔን ማውሳትን
በልብህ ያስዋብኩልህ። ወደ እኛ መዋደቅህ እና እኛን ማውሳትህ በኛ ዘንድ
በፍቅር የመሳብህ ውጤት እንጂ ሌላ አይደለም።
የዝንጉዎችን ልቦችማ! ወደኛ እንዳያስቡ እና ከደጃፋችን እንዳይዋደቁ ግርጆ
አድርገንባቸዋል። በችግሮቻቸውም ግዜ ከደጃፋችን መዋደቅን
አንለግሳቸውም"››

ያ ረብ ከደጃፍህ አዋድቀን!

@yequranbeteseboch

Join it Share it
138 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:41:49 ልቅናችን በነቢ ሰበብ

ሙሳ ዐሰ ተውራትን ሙሉ በሙሉ ካነበበ በኋላ አላህን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ በመጨረሻ የሚመጡ ሲሆኑ ግና ከሁሉም ህዝቦች ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እባክህ የኔ ህዝቦች አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ህግጋቶቻቸውን በልቦቻቻው ሸምድደው ያነበንቡታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ምርኮን ፈቅደህላቸዋል፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ምጽዋትን ይለጋገሳሉ በሱም ትመነዳቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድረጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ጽድቅን ለመስራት አስበው ባይሳካለቸው አንድ ምንዳ ትመዘግብላቸዋለህ፡፡ ከተሳካላቸውም በ10 ታባዛላቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡- ‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ለማመጽ ሲያስቡ ምንም አትመዘግብባቸውም፡፡ ግና ሲያምጹ አንዲትን ብቻ ትመዘግብባቸዋለህ፤ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ የቀደምትን እና የመጺኣንን ትውልዶች ዕውቀት በሙሉ አሸክመኃቸዋል፤ መሲሁ ደጃልንም ይገድሉታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም አለ፡-‹‹ በል እንግድያ እኔንም የሙሐመድ ህዝብ አድርገኛ፡፡››
ሙሳም ንግግሩን ቀጠለ፡-‹‹ ቆይ ግን ጌታዬ ከኔ ህዝብ እሚልቅ ህዝብ አለን››

አላህም አለ፡-‹‹ሙሳ ሆይ በሙሀመድ ህዝቦች እና በሌላው ህዝብ መካል ያለው ልዩነት በኔ እና በፍጥረቴ መከካል እንዳለው ልዩነት እንደሆነ አታውቅምን፡?>>

ሙሳም አለ፡-‹‹እንደው ይኸን የጉድ ህዝብ እንኳን አንዴ አሳየኝ››

አላህም አለ፡-‹‹ልታያቸው አይቻልህም፤ ግና ድምጻቸውን ላሰማህ፡፡››

ከፍጥረት አድማስ ወድያ ከሩሆች ስብስብ ከመናፍስት አለም ያሉ የሙሀመድ ህዝቦችን አላሀ ተጣራ፡፡

ህዝቦችም በአንድ ድምጽ፡-‹‹ለበይከላሁማ ለበይክ›› ይሉ ጀመር።

አላህም አለ፡-‹‹በረከቴ በእናንተ ላይ ይስፈን ፤ እዝነቴ እናንተ ላይ ቁጣዬን ቀደመ ፤ ማርታዬ ስለናንተ ቅጣቴን ቀደመው፡፡

እናንተ ሳትጠይቁኝ አኔ እሰጣችኋለሁ ፤ ከእናንተ ውስጥ የኔን ጌትነት አምኖ በሙሀመድ መለዕክተኝነትም ያመነ መላ ሀጽያቶቹን እሽርለታለሁ፡፡››


ነቢ ልቀው እኛን አላቁን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)


ምንጭ፦
المواهب اللدنية
حلية الأولياء

@yequranbeteseboch

Join it Share it
145 viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:36:09 #ከሙሒቦቹ_አንደበት

የሀ~ያእ~ዐይን~ሷድ (كهيعص) ትርጉም!

ማሊክ ቢን ዲናር (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ አንድ ጊዜ ወደ አላህ ቤት ሐረም ለሐጅ አቀናሁ። መንገድ ላይ ሳለሁ አንድ ሰው ያለ ምንም ስንቅ ሲጓዝ አየሁትና ሰላምታ ሰጠሁት እርሱም መለሰልኝ። ቀጥዬ ከየት ነው የምትመጣው? ብዬ ጠየቅኩት
"ከእርሱ" ብሎ መለሰልኝ
እንዲህ አልኩት፦ ወደ የት መሄድ ፈልገህ ነው?
"ወደ ርሱ ቤት" ብሎ መለሰልኝ
እንዲህ አልኩት፦ የታለ ስንቅህና ጓዝህ?
እንዲህ አለ፦ እርሱ ዘንድ አለኝ!

ጥያቄው ቀጠለ

— ይህ መንገድ ያለ ምግብና ያለመጠጥ አይዘለቅም ምን ይዘሀል?
— አዎን ይዣለሁ። ከሀገሬ ስወጣ አምስት ፊደሎችን ተሰንቄነው የወጣሁት።
— ምንድናቸው እነርሱ?
— የአላህ ቃላት ሲኾኑ በሱረቱል መርየም መጀመሪያ ላይ የሚገኙትን ፊደላት ጠቀሰለት (كهيعص)
— ምን ማለት ነው?
– "ካፍ" ማለት ካፊ (በቂ) ነው፣ "ሀእ" ደግሞ ሀዲ (ቅናቻ መንገድ የሚመራ) ማለት ነው፣ "ያእ" ደግሞ መእዊያ ማለት ሲኾን ስንቅን፣ ምግብን የመሳሰሉ መጠቃቀሚያዎችን የሚያስተናብር ነው። "ዓይን" ደግሞ ዓሊም (ዐዋቂ) ነው ማለት ነው። "ሷድ" ሳድቅ (እውነተኛ) ማለት ነው።
አላህ ቢቂዬ ነው ብሎ በርሱ የተመራ ከእርሱም ስንቅን ከርሱ የጠበቀ እርሱ ደግሞ ዐዋቂና እውነተኛ መሆኑን የተረዳ አይጠፋም አይፈራም። ለጉዞውም ስንቅ ማጣትን አይሰጋም።

ማሊክ እንዲህ አለ፦ ይህን ቃላት ስሰማ ቀሚሴን አውልቄ ላለብሰው ስል እምቢ አለኝና እንዲህ አለ፦ ሸይኽ ሆይ! ቅዝቃዜው ካንተ ቀሚስ ለእኔ መልካም ነው። “ ይህች ዓለም (ዱንያ) ሐላሏ (የተፈቀደ ነገሯ) ሒሳብ ነው። ሐራሟ (የተከለከለ ነገሯ) ደግሞ ቅጣት ነው።”

ለሊቱ ሲጨልም ራሱን ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ እንዲህ ይላል፦

አንተን ብንታዘዝ የማትጠቀመው ብናምጽህ የማትጎዳው ለአንተ የማትጠቀምበትን ሥጠኝ የማትጎዳበትን ምሕረታህን ለግሰኝ።

ሰዎች በሐጅ ለይ "ለበይክ" ሲሉ ይህ ሰው አይለም ነበር። ለምን "ለበይክ" አትልም?

እንዲህ አለ፦ ሸይኽ ሆይ! አላህ ጥሪህንም አልተቀበልኩም ንግግርህን አልሰማም አልመለከትህም። (ላ ለበይክ ወላ ሳዕደይክ ...) እንዳይለኝ ፈርቼ!

ከዚያም ከእኔ ዕይታ ተሰወረብኝ። ሚና ላይ እንዲህ ብሎ በግጥም ስንኝ ሲያለቅስ ግን አየሁት።

إﻥ ﺍﻟﺤﺒﻴﺐ ﺍﻟﺬﻱ ﻳﺮﺿﻴﻪ ﺳﻔﻚ ﺩﻣﻲ -- ﺩﻣﻲ ﺣﻼ‌ﻝ ﻟﻪ ﻓﻲ ﺍﻟﺤﻞ ﻭﺍﻟﺤﺮﻡ""
ﻭﺍلله ﻟﻮ ﻋﻠﻤﺖ ﺭﻭﺣﻲ ﺑﻤﻦ ﻋﺸﻘﺖ -- ﻗﺎﻣﺖ ﻋﻠﻰ ﺭأﺳﻬﺎ ﻓﻀﻼ‌ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻘﺪﻡ""
ﻳﺎ ﻻ‌ﺋﻤﻲ ﻻ‌ ﺗﻠﻤﻨﻲ ﻓﻲ ﻫﻮﺍﻩ ﻓﻠﻮ -- ﻋﺎﻳﻨﺖ ﻣﻨﻪ ﺍﻟﺬﻱ ﻋﺎﻳﻨﺖ ﻟﻢ ﺗﻠﻢ""
ﻳﻄﻮﻑ باﻟﺒﻴﺖ ﻗﻮﻡ ﺑﺠﺎﺭﺣﺔ --ولو بالله ﻃﺎﻓﻮﺍ ﻷ‌ﻏﻨﺎﻫﻢ ﻋﻦ ﺍﻟﺤﺮﻡ""
ﻟﻠﻨﺎﺱ ﺣﺞ ﻭﻟﻲ ﺣﺞ ﺇﻟﻰ ﺳﻜﻨﻲ -- ﺗﻬﺪى الأ‌ﺿﺎﺣﻲ ﻭأﻫﺪﻱ ﻣﻬﺠﺘﻲ ﻭﺩﻣﻲ


ከዚያም እንዲህ አለ

ጌታዬ ሆይ! ሰዎች በዕርድና በሰጠሀቸው ነገር ወደአንተ ለመሄድና ተቃረቡህ። እኔ በነፍሴ እንጂ ወደ አንተ የምቃረብበት ነገር የለኝምና ተቀበለኝ። ከዚያም ወደ ሰማይ እየተመለከተና በብርቱ ሆኔታ እያለቀሰ ወደ አላህ ዘንድ በሞት ተሻገረ። አላህ ይዘንለት።

ይህን ለሊት ይህን ጉዳይ እያሰብኩ በሕልሜ አገኘሁትና ጠየቅኩት ይላሉ ታሪኩን የሚዘግቡልን ታላቅ ሰው።

አላህ በአንተ ላይ ምን አድርጎ ነው?

እንዲህ አለኝ፦ በበድር ዕለት የተሰዉት ላይ እንዳደረገው። ለእኔ ግን ከዚያም በላይ ጨመረልኝ።

ምንድነው ጭማሬው? ሰል ጠየቅኩት

እንዲህ አለ፦ እነርሱ የተገደሉት በከሐዲያን ሰይፍ ሲኾን እኔ ግን የተገደልኩት በጀባር መሐባ ነው።

(ረውድ አል ሪያሒይን)

ኢማሙ ሻፍዒይ (ራ.ዐ)

አላህ ሙሒቦች ከቀመሱት ያቅምሰና

@yequranbeteseboch

Join it Share it
116 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 22:20:03 []ሱጁድ[]
ግንባር እመሬት
ልብ ሰማይ ላይ!
–በውስጥህ የቋጠርካቸውን ሚስጥሮች ሱጁድ ላይ በትናቸው!
–ለማን እየሰገድክ እንደሆነ ብታቅ ሱጁድህን ባስረዘምክ ነበር
ሱጁድ ላይ
በአካል ወደ መሬት ዝቅ ብለህ
በመንፈስ ወደ ጌታህ ትቀርባለህ
_
ነፍስ ተጠባ ከሁሉ ነገር ስትሸሽና ስትርቅ
ከሱጁድ ውጪ ምትረጋበትን ታጣለች!
★ልብህ ሲጨነቅ ሱጁድ አድርግ
★አሳብህ ሲበታተን ሱጁድ አድርግ
★ሁኔታህ ሲቀያየር ሱጁድ አድርግ
{ولقد نعلم أنك يضيق صدرك بما يقولون*فسبح بحمد ربك وكن من الساجدين}
[አንተም በሚሉት ነገር ልብህ እንደሚጠብ በእርግጥ እናውቃለን*ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፣ከሰጋጆቹም ሁን]
አል ሂጅር/97–98)

የሌሊት ሱጁዶች የቸልተኝነትን ግርዶሽ ገፈው
ወደ አላህ መአድ ያቀርባሉ!

ሁሌም ሱጁድን አብዛ፣ከጌታህ ጋር ተነጋገር፣ሚስጥርህን አጋራው፣መፀፀትህን ንገረው፣ደካማነትህን አሳየው
ያኔ ካለህበት ጭንቀት መውጫ ቀዳዳ ያበጅልሃል
=====

@yequranbeteseboch

Join it Share it
215 views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:22:35 ሰኢድ ቢን አሚር ለኡመር ኢብኑ አል ኸጣብ ከመከረው
ምክር መሃከል :

“ኡመር ሆይ!
በሰዎች ጉዳይ ላይ አላህን ልትፈራ አደራ እልሃለው
በአላህ ጉዳይ ላይ ግን ሰዎችን
ልትፈራ አይገባም ንግ ግርህም ተግባርህን እንዳይቃረን
ከንግግሮች ምርጥ
የሚባለው ተግባር እውን ያደረገው ነው … በአላህ ጉዳይ
ላይ የወቃሽን ወቀሳ
እንዳትፈራ”

@yequranbeteseboch

Join it Share it
250 viewsedited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:43:00
የምታዩት ደስ የሚል ቀደምት የቱርክ ሃገር ልማድ ነው:‐
መስጂድ ውስጥ፣ በመንገድ ላይ፣ በቤት ውስጥ ወይም በማንኛውም ቦታ
የተፈቃሪው [ ﷺ ] ስም ሲጠራ እጃቸውን ልባቸው ላይ ይለጥፋሉ።
ይህንን የሚያደርጉበት የሚደንቅ ምክንያት አላቸው።…
የነቢዩ [ ﷺ ] ሥም ሲጠራ የሙእሚን ቀልብ ከቦታው ተነስቶ በናፍቆት ክንፍ
ሊበር ይደርሳል። ስለዚህ ሰውየው እጁን በልቡ ላይ አድርጎ ያረጋጋዋል።
በተናፋቂው ሐውዳቸው ላይ እስከሚያገኛቸው ድረስ እንዲታገስ ያባብለዋል!
ዐጂብ ነው!…
:
በኑሩ ምድር፣ ከጀነቱ ጨፌ፣ በሸፊዓችን [ ﷺ ] አቅራቢያ ያላችሁ ሰዎች
ታድላችኋልና በዚያራችሁ ላይ አስታውሱን። ምርጣችንን ሰልሙልን!

አላሁመ ሰሊ ወሰልም ወባሪክ ዐላ ሰይዲና #ሙሀመድ

@yequranbeteseboch

Join it Share it
277 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:29:08 የዱዓ ኢስቲጃባ በረቡዕ ቀን
=================

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ [ረዲየላሁዐንሁ] እንደዘገቡት: ‐ «ነቢዩ [ﷺ] መስጂዱል‐ፈትሕ ውስጥ ሦስት ጊዜ ዱዓእ አደረጉ። ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ። በረቡዕ እለትም በሁለቱ ሶላቶች መካከል ዱዓቸው ኢስቲጃባ [ተቀባይነት] አገኘ። በፊታቸው ላይም ብስራት ታየ።»
የኢማም በይሀቂይ "ሹዐቡል‐ኢማን" ላይ እንደተጠቀሰው በሁለቱ ሶላቶች መካከል ማለት በዙህር እና በዐስር መካከል ማለት ነው።
:
ጃቢር እንዲህ ይላሉ: ‐ «እጅግ አሳሳቢና ከባድ ነገር ሲገጥመኝ ይህንን ሰዓት ጠብቄ ዱዓ አደርጋለሁ። ተቀባይነት እንደሚያገኝም አውቃለሁ።» ኢማም ቡኻሪይ ''አደቡል‐ሙፍረድ'' ላይ ዘግበውታል።

@yequranbeteseboch

Join it Share it
239 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:36:27
የአምልኮ አምላኪ ....!!!
_____\\\__\\\\_____
ፍቅርን ኖረው ካስተማሩ፤አላህን አውቀው ካሳወቁ አያሌ ድንቅ ባሮቹ ውስጥ አንዱ የሆኑት አቡ የዚድ አል ቡስጣሚ(ረሕመቱላሂ ዐለይህ) ዘንድ ውስን ሰዎች መጥተው
[አላህን እንገዛለን፤ግን እንደው የአምልኮውን ለዛ(እርካታ) ለምን ይሆን የማናገኘው? ]ሲሉ ይጠይቋቸዋል፤አቡ የዚድም በመንገዱ ብዙ የለፉ፣ባለፉበት ያለፉ፣የጉዞውን እንከንና ፈውስ አብጠርጥረው የተረዱ ዓሪፍ ስለነበሩ ክፍተቱ ምን ጋር እንዳለ ነገሯቸው
" የዒባዳዎችን ጥፍጥና ማታገኙበት ምክንያትማ እናንተ አምልኮዎችን እንጂ አላህን አልተገዛችሁም፤በዛ ላይ ከፍቅሩ በተነጠለች ልብ ነው የተገዛችሁት፤ለሱ ቀረቤታ፣ትስስርና ውዴታ ብላችሁ አልሰራችሁም፤ሶላታችሁ ትእዛዙን ለመፈፀም ብቻ የሚደረግ እንቅስቃሴ አታድርጉ፤ሶላት ማለት ከሱ ጋር መገናኛ መስመራችሁ፣የሩሓችሁ መሰላልና ወደሱ መላቂያዋ ነው"በማለት መለሱላቸው።
_____
መደ ያ ረብ!!!

@yequranbeteseboch

Join it Share it
316 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ