Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ ሴኔት ቲክቶክን በአገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ! የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር | YeneTube

የአሜሪካ ሴኔት ቲክቶክን በአገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ!

የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በአገሪቱ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል አወዛጋቢ አዋጅን አጽደቀ።አዋጁ የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ የማህበራዊ ትስስር ገጹን ድርሻ በ9 ወር ውስጥ የማይሸጥ ከሆነ ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ ያግዳል።አዋጁ ወደ ፕሬዝዳንት ባይደን የተመራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አዋጁ ኋይት ሃውስ እንደደረሰ ፊርማቸውን አኑረውበት ሕግ እንደሚያደርጉት ተናግረው ነበር።

ባይትዳንስ ለዚህ ውሳኔ ፈጣን መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ለቢቢሲ ተናግሯል።ቀደም ብሎ ግን ቲክቶክ በጫና ለማሸጥ የሚደረግ ሙከራን አጥብቆ እንደሚቃወም ተቋሙ ገልጿል።አሜሪካ ቲክቶክን እንዲሸጥ ባይትዳንሳ ላይ ጫና አድረጋ ቢሳከላት እንኳን ለሽያጩ ሂደት የቤጂንግ ባለስልጣናት ይሁንታ ያስፈልጋል።ሆኖም ቻይና ይህንን አይነቱን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጻለች።

ተንታኞች ይህ ሂደት ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ይገልጻሉ።ይህን አዋጅ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት አብለጫዎቹ ደግፈውታል።79 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 18 የሚሆኑት ደግሞ ተቃውመውታል።

የምክር ቤት እውቅ የሪፐብሊካን እና የደህንነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለአመታት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በአሜሪካ ዝነኛ የሆነውን መተግበሪያ እንዲቆጣጠረው ፈቅደናል። ይህ ሁኔታ በአደገኛ ሁኔታ የቅርቡን ብቻ የተመለከተ ነው” ብለዋል።ጨምረውም አዲሱ አዋጅ ቻይናውያን ባለቤቶቹ መተግበሪያውን እንዲሸጡ የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቅሰው ለአሜሪካ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa