Get Mystery Box with random crypto!

ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል | YeneTube

ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa