Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በፖለቲካ ኦፊሰሩ አቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በአፋጣ | YeneTube

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በፖለቲካ ኦፊሰሩ አቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በአፋጣኝ እንዲመረምሩ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጥያቄ አቀረበ። አቶ በቴ በመቂ ከተማ የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት መሆኑን ኦነግ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ገልጿል።

ኦነግ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፤ የአቶ በቴን ሞት “ጭካኔ የተሞላበት ግድያ” ሲል ጠርቶታል። ፓርቲው በፖለቲካ ኦፊሰሩ ላይ ግድያ መፈጸሙን ቢያረጋግጥም፤ የድርጊቱን ፈጻሚዎች በተመለከተ በመግለጫው ላይ ያለው ነገር የለም። ሆኖም ግድያውን በተመለከተ  ተጨማሪ ምርመራዎች እያደረገ መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል።

Via:- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@Yenetube @Fikerassefa