Get Mystery Box with random crypto!

ጋና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ጠንካራ ሕግ አጸደቀች! የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ | YeneTube

ጋና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ጠንካራ ሕግ አጸደቀች!

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጸደቀ።አዲሱ ሕግ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስር፣ ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ አምስት ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል።

የአገሪቱ ሕግ አውጪዎች የእስር ቅጣቱ ወደ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና የምክር ድጋፍ እንዲቀየር የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ውድቅ አድርገውታል።በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው።ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አብዛኛው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉት ከሆነ ሕጉን እንደሚያጸድቁት ተናግረው ነበር።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በጋና ውስጥ ቀደም ብሎም ሕገወጥ ሆኖ በሦስት ዓመት እስር የሚያስቀጣ ነው።ሕጉ “በሰዎች መሠረታዊ መብት እና ነጻነት ላይ ከባድ አደጋን የሚደቅን ነው” ሲል ባለፈው ወር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞውን አሰምቶ ነበር።የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብት ተቆርቋሪዎች አሁን የወጣው ሕግ ሰዎችን እና በዚህ ዙሪያ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማሳደድ ስለሚውል አንዳንዶች ለመደበቅ ይገደዳሉ ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa