Get Mystery Box with random crypto!

በሕንድ የባቡር አደጋ ከ280 በላይ ሰዎች ሞቱ! በሕንድ ምሥራቃዊ ኦዲሻ ግዛት፣ ባላሶሬ በሚባል | YeneTube

በሕንድ የባቡር አደጋ ከ280 በላይ ሰዎች ሞቱ!

በሕንድ ምሥራቃዊ ኦዲሻ ግዛት፣ ባላሶሬ በሚባል አውራጃ ሁለት በተለያየ መስመር የሚዘወሩ ባቡሮች ተላትመው 288 ተሳፋሪዎች ሲሞቱ 850 የሚሆኑት ቆስለዋል።አደጋውን ተከትሎ 200 አምቡላንሶች ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ ሲሆን ከአደጋው የተረፉ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን ሌሎችን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋል።

አደጋው የደረሰው ትናንት ዐርብ ሲሆን አንድ የመንገደኞች ባቡር መስመሩን ስቶ ከወጣ በኋላ በሌላ ከተቃራኒ አቅጣጫ እየከነፈ ይመጣ በነበረ ባቡር መገጨቱን ተከትሎ ነው በርካታ ሰዎች ሊጎዱ የቻሉት።

ይህ አደጋ በሕንድ በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን ከደረሱ የባቡር አደጋዎች የከፋው ነው ተብሏል።የአካባቢው ባለሥልጣናት የሟቾች ቁጥር አሁን ካለበት በብዙ ሊያሻቅብ እንደሚችል ሰግተዋል።የሕንድ የባቡር አስተዳደር እንዳለው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ኮሮማንዴል ኤክስፕረስ እና ሆውራሽ ሱፐርፋስት ኤክስፕረስ ባቡሮች ናቸው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa