Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የወረዳ አመራሩ በፖሊስ ተገደሉ! በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ | YeneTube

በአዲስ አበባ የወረዳ አመራሩ በፖሊስ ተገደሉ!

በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለባቸው አሞኜ በዛሬው ዕለት በቢሮአቸው ሥራ ላይ እንዳሉ ተገደሉ።የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ ተገልጋይ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል" ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ፣ "በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በፖሊስ አባል ተገድለዋል" ብሏል፡፡

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የፖሊስ አባሉ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት አመልክቶ ለጉዳዩ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚን ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ እንደገደላቸው መታወቁን አብራርቷል።ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአመራሩ መገደል ማዘኑንም አስታውቋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa