Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እ | YeneTube

የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው - መንግሥት

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ

የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው።

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ኅዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽሬ ላይ ሥራውን ጀምሯል።ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች

የተወጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ ይሆናል።

ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮችምክንያትመዘግየቱ ይታወቃል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@YeneTube @FikerAssefa