Get Mystery Box with random crypto!

የታጠቁ ኃይሎች በሰላም አፈላላጊዎች ጥረት ወደ ምክክር ሊመጡ እንደሚችሉ ተገለጸ! የኢትዮጵያ አ | YeneTube

የታጠቁ ኃይሎች በሰላም አፈላላጊዎች ጥረት ወደ ምክክር ሊመጡ እንደሚችሉ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የታጠቁ ኃይሎች በሰላም አፈላላጊዎች ጥረት ወደ ምክክር ሊመጡ እንደሚችሉ አስታወቀ።ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን የሥራ አፈጻጸሞች አስመልክቶ ትናንት ኀዳር 21/2015 መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም የታጠቁ ኃይሎችን ወደ ምክክሩ ለማምጣት መንግሥት የሚሰራው ሥራ አለ ያለ ሲሆን፤ የታጣቁ ኃይሎች በመንግሥት በኩል በሚሰሩ ሥራዎች፣ በሰላም አፈላላጊዎች እንዲሁም በአገር ሽማግሌዎች ጥረት ወደ ምክክሩ ይመጣሉ የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በመገባደድ ላይ በሚገኘው በዚህ ወር ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀውን ምክክር አራዝሟል፡፡ ኮሚሽኑ የምክክር አጀንዳዎችን ከሕዝብ ሰብስቦ ከቀረጸ በኋላ፣ በ2015 አጋማሽ ምክክር እንደሚጀመር የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጠቁመዋል፡፡ በምክክሩ ሂደቱ ማንኛውም የማኅበረሰብ ክፍል ሳይወከል እንዳይቀር ኮሚሽኑ አበርክሮ እንደሚሰራም ጠቁሟል፡፡የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክክሩን አካታች የማድረግ ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ሲሆን፣ የታጠቁ ኃይሎች በአገራዊ ምክክሩ ሊሳተፉ የሚችሉት ትጥቅ ፈተው ወደ ውይይት ከመጡ ነው የሚል አቋም አለው፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa