Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት ለውጭ ባንኮች የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ በቁጥር የተገደበ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ መንግ | YeneTube

መንግሥት ለውጭ ባንኮች የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ በቁጥር የተገደበ እንደሚሆን ተነገረ፡፡

መንግሥት ባፀደቀው ፖሊሲና ይህንን ተከትሎ በተረቀቀው የባንክ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ መሠረት፣ ለውጭ ባንኮች የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ በቁጥር የተገደበ ይሆናል ተብሏል፡፡

ሪፖርተር አገኘሁት ያለዉ የፖሊሲ ሰነድና ይህንን ሰነድ መነሻ አድርጎ የተረቀቀው የባንክ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ እንደሚጠቁመው፣ መንግሥት ለረዥም ዓመታት ዝግ የነበረውን የአገር ውስጥ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ክፍት ሲያደርግ የሚመጡትን የውጭ ባንኮች በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ የሚሰጥ አይሆንም።
ይልቁንም ልክ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ውድድር ክፍት ሲያደርግ፣ ለሁለት የውጭ ቴሌኮም ኩባንያዎች ብቻ ፈቃድ ለመስጠት እንደወሰነው ሁሉ፣ የባንክ ዘርፉንም ለውጭ ውድድር ክፍት ሲያደርግ ለመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት ፈቃድ የሚሰጠው ለተወሰኑ የተመረጡ የውጭ ባንኮች እንደሚሆን ሰነዶቹ ያመለክታሉ።

በፀደቀው የፖሊሲ ሰነድ መሠረት ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት የኢትዮጵያ ንዑስ ባንክ ለማቋቋም የሚጠይቁና የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ለማቋቋም የሚጠይቁ የውጭ ባንኮች ናቸው።

በመሆኑም በተጠቀሱት ሁለት የባንክ ሥራ ዓይነቶች በእያንዳንዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ ከአምስት እንደማይበልጥ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የባንክ ፖሊሲ በግልጽ አመላክቷል።
‹‹አዲስ ፈቃድ ከመስጠት አንፃር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከሦስት እስከ አምስት ፈቃድ ለውጭ ባንኮች ሊሰጥ ይችላል ተብሏል።

በተመሳሳይ ቅርንጫፍ መክፈት ለሚፈልጉ ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ብቻ ሆኖ፣ እያንዳንዳቸው መክፈት የሚችሉት የቅርንጫፍ ብዛትም ከሁለት እስከ አራት ቅርንጫፎችን ብቻ ይሆናል›› ሲል የፖሊሲ ሰነዱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

@Yenetube @Fikerassefa