Get Mystery Box with random crypto!

የሰቆጣ፣ ላሊበላ፣ ቆቦ እና ሮቢት አካባቢዎች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኛሉ ተ | YeneTube

የሰቆጣ፣ ላሊበላ፣ ቆቦ እና ሮቢት አካባቢዎች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኛሉ ተባለ!

ከአላማጣ የማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኙ የአማራ እና የትግራይ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እስከ ነገ ማክሰኞ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሰው እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።በደቡባዊ ትግራይ ዞን የምትገኘው የአላማጣ ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የአገልግሎቱ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

እንደ አቶ መላኩ ገለጻ ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለው የመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።“ከአላማጣ ቆቦ ባለው መስመር የዛፍ ቅርንጫፎችን መመንጠርና አገልግሎቱን የማስጀምር ስራ ነው የቀረው” ሲሉ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

አቶ መላኩ አክለውም “ከተቻለ እና ይሄ ከተጠናቀቀ ሮቢትን ጨምሮ ቆቦ እና አካባቢው ዛሬ ምሽት የኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሰው እንዲያገኙ እየሰራን ነው” ብለዋል።በተመሳሳይ ከአላማጣ የማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኙ የሰቆጣ እና የላሊበላ አካባቢዎችም ዛሬ ምሽት ኃይል ያገኛሉ ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa