Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መል | YeneTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደስታ መግለጫቸው፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

በሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰፊ የድምፅ ልዩነት ያሸነፉት ሀሰን ሼክ መሃመድ ምርጫው በተጠናቀቀ ጥቂት ሰአታት ውስጥ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

ለሁለት ዓመታት የተራዘመው የሶማሊያ ምርጫ በትላንትናው እለት ተካሂዶ አገሪቱን ለቀጣይ 4 አመታት የሚመሩት ሀሰን ሼክ መሃመድ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በ3ኛው ዙር 328 ድምፅ ያለው የሶማሊያ ፓርላማ ባደረገው ምርጫ ሀሰን ሼክ መሃመድ በስልጣን ላይ ያሉትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን ካጠቃላዩ ድምፅ የ214ቱን በማግኘት ነው ለማሸነፍ የበቁት።

የሶማሊያው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከዚህ ከቀም በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2017 ሶማሊያን በፕሬዝዳንትነት መርተው እንደነበረ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa