Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ስታዲየም ይገጥማል! የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ | YeneTube

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ስታዲየም ይገጥማል!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል።

ቀደም ሲል ለኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የተመረጠው የባህርዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃን ባለማሟላቱ ካፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምታደርገውን ጨዋታ በሌላ ሀገር ስታዲየም እንድታደርግ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በመሆኑም ካፍ ኢትዮጵያ የማጣሪያ ጨዋታዋን የምታደርግበትን ስታዲየም እንድታሳውቅ መጠየቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከግብፅ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሚጫወትበትን ስታዲም አሳውቋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በቀድሞው የማላዊ ፕሬዝዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ስም በተሰየመው ቢንጉ ስታዲየም ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa