Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮ | YeneTube

የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ ያቀረበውን አቤቱታ ላለማየት መወሰኑን ተዘግቧል።

የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ አልወያይበትም ብሎ ወደ ጎን የገፋው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴዎድሮስ የአማጺው ሕወሃት ደጋፊ እንደሆኑ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሐሰተኛ መረጃ እንደሚያሰራጩ ጠቅሶ የድርጅቱ የበላይ ቦርድ ምርመራ እንዲያደርግባቸው ያቀረበውን አቤቱታ ነው። ቦርዱ ይህን ያሳወቀው፣ በዶ/ር ቴዎድሮስ ሁለተኛ ዙር የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዕጩነት ላይ ለመወያየት ዛሬ በጀኔቫ ባደረገው ስብሰባ ላይ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ፣ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው እና ከቦርዱ አሠራር ውጭ እንደሆነ ኬንያዊው የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት 34 አባላት ላሉት ቦርድ የተናገሩ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከቦርዱ ይልቅ ሌላ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ቢመለከተው ይሻላል በማለት ያቀረቡትን ሃሳብ ቦርዱ ያለ አንዳች ተቃውሞ ተቀብሎታል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa