Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰዎች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ሲሉ የከሚሴ ከተማና አካ | YeneTube

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰዎች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ሲሉ የከሚሴ ከተማና አካባቢው አንዳንድ ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡

ለደህንነታቸው ስማቸው እንዳይገለፅና ድምፃቸውም እንዳይቀረፅ ያስጠነቀቁት አስተያየት ሰጪዎች ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ ሰዎች በፖሊስ እየተያዙ እየታሰሩ ነው ብለዋል፡፡የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዲ እንደሪስ ያለምክንያት የታሰረ ሰው የለም፣ በቅርቡ ከነበረው የህወሓት ወረራ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ግን አረጋግጠዋል፡፡

የማጣራት ሥራው የተለየ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያነጣጠረ አይደለም ያሉት አቶ አብዲ እስሩ “የሐይማኖት አባቶችን ያነጣጠረ ነው” የሚለውን ስምታ አይቀበሉም። ምን ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለመናገር ፈቃደኛ ያልሆኑት አቶ አብዲ ህብረተሰቡ ከአሉባልታ ወሬ ይቆጠብ ሲሉም መክረዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa