Get Mystery Box with random crypto!

የኢሰመኮ ዓለም አቀፍ ተአማኒነት በመጀመሪያ ደረጃ ከሚመደቡት ውስጥ ተካተተ! የተባበሩት መንግሥታ | YeneTube

የኢሰመኮ ዓለም አቀፍ ተአማኒነት በመጀመሪያ ደረጃ ከሚመደቡት ውስጥ ተካተተ!

የተባበሩት መንግሥታት ባጸደቀው "የፓሪስ መርኆዎች" በተሰኘው መለኪያ መሰረት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተአማኒነቱ ወደ ከፍተኛው ደረጃው 'ኤ' እንዲገባ ዓለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት መወሰኑ ይፋ ተደረገ።ጥምረቱ በመላው ዓለም ያሉ 118 ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማትን በአባልነት ያቀፈና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በፀሐፊነት የሚመራው ስብስብ ነው።

የፓሪስ መርኆዎች እንደ ኢሰመኮ ያሉ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ተቋማት ከሚሰሩባቸው ሕጎች፣ ከዕለት ተለት እንቅስቃሴያቸው፣ ከፖሊስ፣ ከአባልነት እንዲሁም በሚያንቀሳቅሱት ንብረት ላይ ካላቸው የማስተዳደር ሥልጣን በመነሳት ገለልተኛና ራሳቸውን ችለው የቆሙ መሆናቸውን የሚመዝን ሰነድ ነው።በዚህም መሰረት ኢሰመኮ ለጥምረቱ የእውቅና ንዑስ ኮሚቴ ባለፈው ጥቅምት ወር ባቀረበው የጥያቄ ማመልከቻ መሠረት አዲሱ ደረጃ እንደተሰጠው የመብት ተቋሙ ጠቅሷል።

"ጥምረቱ ኢሰመኮ ሰብአዊ መብቶችን ለመከላከል እና ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት ብሎም ከስምንት ዓመታት በፊት በነበረው ግምገማ ወቅት ይሻሻሉ የተባሉ ነጥቦችን በማሻሻሉን እንደሚያበረታታ ገልጿል" ሲል በመግለጫው አመልክቷል።በፓሪስ መርኆዎች መሰረትም አንድ ተቋም ባለው ሥልጣን እና ሥልጣኑን የሚተገብርበት አቅም፣ አካታችነት፣ ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት፣ ብሎም ከአህጉራዊና ከዓለም አቀፋዊ ተቋማት ጋር ያለው ሥራ ግንኙነት ተጨማሪ መለኪያዎች ናቸው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa