Get Mystery Box with random crypto!

ከሚሴን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጥተዋል - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎ | YeneTube

ከሚሴን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጥተዋል - የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከሚሴን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ማውጣቱን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በ"ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" ባካሄደው ኦፕሬሽን፣ የተለያዩ ከተሞችን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ የማውጣቱን እና በጥልቀት በመግባት የአሸባሪውን ጀሌዎች የመማረክ እና የመደምሰስ ተግባሩን ቀጥሏል።

በዚህም መሠረት በጋሸና ግንባር ቀውዝባና ጭላ ከተሞችና አካባቢያቸው ከአሸባሪው ኃይል ነጻ የወጡ ሲሆን፣ በወረኢሉ ግንባር በተደረገው ኦፕሬሽን ደግሞ አጅባር፣ ተንታ እና ዶባ ከተሞች እና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በተያያዘም፣ በከሚሴ ግንባር ማጀቴን፣ ጭረቲን፣ ከሚሴን፣ ርቄን፣ ወለዲን፣ አልቡኮ ከተሞችን እና የቃሉ ወረዳን አብዛኛውን ክፍል በመቆጣጠር፣ ጥምር ጦሩ ወደ ኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ይገኛል።

ዛሬ እና ትናንት በተደረጉት ከፍተኛ የማጥቃት ኦፕሬሽኖች አብዛኛው የአሸባሪው ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲበተን ተደርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa