Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አሳለፈ! | YeneTube

ትምህርት ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አሳለፈ!

የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመወያየት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሀሳቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ የሁሉንም ዜጋ ኀላፊነት እና ትብበር የምትፈልግበት በመሆኑ ከሕዳር 27 እስከ ታህሳስ 3/2014 የመማር ማስተማሩ ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በጦርነቱ የዘማች አርሶ አደሮችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦችን በመርዳት ትብብር እንዲያደርጉ ወስኗል፡፡

ለዘመቱ አካላት የሚሆን የስንቅና የደም ልገሳ በማድረግም የዜግነት ግዴታን የምንወጣበት ጊዜ ነው፤ ተማሪዎች ትምህርት በሚቋረጥበት ጊዜ ከትምህርታቸው ሳይዘናጉ የወገን ጦርን የሚረዱበትና የአገር ፍቅራቸውን የሚያሳዩበት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa