Get Mystery Box with random crypto!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገብረ መድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት | YeneTube

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገብረ መድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰረዝ ወሰነ!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29/ 2005 ዓ.ም ለዶ/ር ኢሌኒ ገ/መድኅን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt) የሰጣቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ዶ/ር ኢሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲው ለዶ/ር ኢሌኒ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤን እና ሲመረምር መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 4 እና በዩኒቨርሲቲው የሴኔት ደንብ አንቀጽ ቁጥር 6 ንዑስ አንቀጽ 16 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድሕን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt) እንዲሰረዝ መወሰኑን ገልጿል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa