Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቡና መሸጫ ዋጋ ከባለፈው ዓመት የ58 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ! የኢትዮጵያ ቡና መ | YeneTube

የኢትዮጵያ ቡና መሸጫ ዋጋ ከባለፈው ዓመት የ58 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ ቡና መሸጫ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ58 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገለጸ።ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ቡና የመሸጫ ዋጋው አንድ ኪሎ 3.3 ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት የጥቅምት ወር የተሸጠበት ዋጋ ደግሞ ወደ 5.3 ዶላር ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል። የመሸጫ ዋጋው ጭማሪ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የኹለት ዶላር ዕድገት አሳይቷል።

‹ዋይ ቻርት የፋይናንስ ሶፍትዌር እና መዋዕለ ንዋይ ጥናት ተቋም› ባወጣው ጥናት፣ የኢትዮጵያ ቡና (ኮፊ አረቢካ) ባለፈው የጥቅምት ወር የመሸጫ ዋጋው በኪሎ 5.3 ዶላር መድረሱን ጥናቱ አስቀምጧል።ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ በ2012 የአንድ ኪሎ የኢትዮጵያ ቡና የመሸጫ ዋጋ 2.8 ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በኹለት ዓመት ውስጥ የመሸጫ ዋጋ የ2.5 ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa