Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም ህብረተሰብ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት!!”፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በ | YeneTube

ሁሉም ህብረተሰብ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት!!”፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በግንባር እና በተወረሩ አካባቢዎች የሚገኙ ሁሉም ህብረተሰብ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የህልውና ዘመቻ ወደ ተሟላ የማጥቃት እርምጃ እንደገባ ያስታሰወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወራሪው ቡድን ለአብነት በጭፍራ በመስኪዶች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ጠቁመዋል።

የሽብር ቡድኑ የኃይማኖት ቅዱሳን ቦታዎችን በማርከስ፣ የኃይማኖት መፅሀፍቶችን በማቃጠል እና ውድመት በመፈፀም እና የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ስነ-ስቦናዊ ጫና ለማድረግ አቅዶ መንቀሳቀሱን አስታውቀዋል።

ጠላት በወገን ጦር ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት እንደሚገኝ ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ አሸባሪው ቡድን ሲሸሽ በህብረተሰቡ ውስጥ ገብቶ እንዳይሸሸግ ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ነቅቶ እንዲጠብቅም ነው ያሳሰቡት።

ህብረተሰቡ ሰራዊቱን በጠንካራ ደጀንነት እየደገፈ እንደቀጠለ እና አሁንም በዚሁ መልኩ ህብረተሰቡ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa