Get Mystery Box with random crypto!

መስሎኝ ነበር @onitwa እንደማታፈቅረኝ አውቅ ነበር። አብረን እንደማንሆንም አውቅ ነበር። | 🌷💘🌹ፍቅርና💞ጥበብ💖💘

መስሎኝ ነበር

@onitwa

እንደማታፈቅረኝ አውቅ ነበር። አብረን እንደማንሆንም አውቅ ነበር። ሌላ ሴት ልታፈቅር እንደምትችልም አውቅ ነበር።

እነዚህን ቃላቶች እንደምሰማቸውም አውቅ ነበር።
አንተም ታውቅ ነበር፤ ስትነግረኝ እንደሚከፋኝ ፣እንደሚደብረኝ፣ ውስጤ እንደሚታመም፣ጠንካራ እንዳልሆንኩ፣ @onitwa ደስተኛ እንደማልሆን ፣ተከፍቼ እንደማልነግርህ፣ ልቤ ተሰብሮ ልታፅናናኝ እንደማትችል ታውቅ ነበር።

አሁን ሲገባኝ ቀድመህ ልታዘጋጀኝ እየሞከርክ ነበር፤ሲከፋኝ የማቅፈውን እንዳገኝ ስትጥር ነበር ልቤ እንዳይደሞ በብዙ ስትለፋ ነበር።

እኔም ጠንካራ እንደሆንኩ ነግሬህ ነበር። ውስጤን እንዳሳመንኩት ነግሬህ ነበር አልጎዳምም ብዬህ ነበር። የምርም እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር... ታዲያ አሁን ለምን ውስጤን ያመኛል? ለምን የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል? @onitwa

ያን ቀን ደስተኛ ነበርኩ የእኔ ሁሉ ነገር ስትለኝ አለም ጠባኝ ነበር። የእኔ ንግስት ስትለኝ ለደስታዬ ጥግ አጥቻለሁ... ስታቅፈኝ ዓለሜን ባንተ እቅፍ ሸሽጌአለሁ...

አሁን ልቤን በጥልቁ ያመኛል። ልፅፈው አልቻልኩም መናገርም አቅቶኛል ማልቀስም ፈልጌ ሳግ ተናንቆኛል፤ ታውቃለህ ይህ ስሜት ከዚህ በፊት በጥልቅ ስቃይ ሳይሆን በመናፈቅ ውስጥ ተሰምቶኝ ነበር፤ልናገረው ልፅፈው ያልቻልኩት የናፍቆት ሳይሆን የህመም ስሜት... @onitwa አውቃለሁ ደስታህ ሊያስደስተኝ ይገባ ነበር። ዓለምህ ዓለሜ ሊሆን ይገባኝ ነበር፤እንደዛም እንደሚሆን ጠብቄ ነበረ...

ቃሎች ከአፍህ ሲወጡ ይታወሰኛል... ስለምታፈቅራት ልጅ አቅፈህ በደስታ ፊትህ እያበራ ስትነግረኝ ምስሉ ይታየኛል... @onitwa ልብህ ስትቦርቅ ይሰማኛል .... ብታውቂያት ትወጃታለሽ አልከኝ አንተ ወደሃት እኔ ልጠላት እንደማልችል ታውቃለህ... ደጋግመህ እንዳልደበረኝ ጠየከኝ በጭራሽ አልኩህ አልዋሸሁም የእውነቴን ምንም አልተሰማኝም ነበር... ደቂቃዎች በሰዓት ሲተኩ ውስጤ በረዶ መሆን ጀመረ።

ጥልቅ ዝምታ ... @onitwa አሁን የሚሰማኝን ተወው ልነግርህ የምፈልገው የጠነከርኩ ፣እውነቱን መጋፈጥ የምችል፣ ተስፋ የቆረጥኩ፣ ደስተኛ የምሆን፣ የማይከፋኝ መስሎኝ ነበር። ለካ እውነታው ከባድ ነበር።

ተፃፈ በኦኒ

6/7/2014 ዓ.ም

ሼር ሼር

@onitwa

@onitwa