Get Mystery Box with random crypto!

#እጠብቅሻለሁ ሁሌ እን'ዳዲስ.. ትመጫለሽ ብየ በሰፊው ጎዳና መንገዱን ስጠርግ እዉላለሁ መንገዱ | 💖የኔ ፍቅር 😘

#እጠብቅሻለሁ

ሁሌ እን'ዳዲስ..
ትመጫለሽ ብየ በሰፊው ጎዳና
መንገዱን ስጠርግ እዉላለሁ መንገዱን ሳቃና
ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ሰንጥቀሽው ትመጭ እንደው እላለሁ
የዝናብ ልብስና መጠለያ ይዤ መንገዱን አያለሁ
ደግሞ ጠራራዋ ፀሃይ በረድ እስክትል ሳትጠብቂ
ትመጭ ይመስል ድጋሚ ከኔ ጎን ላትርቂ
በተስፋ ታድሸ ሁሌ እጠብቅሻለሁ
ምን እንዳስነካሽኝ እኔስ ምን አዉቃለሁ
ብቻ የክረምቱንም ቸነፈር የበጋዉን ወላፈን ሳትፈሪ
ተስፋ አለኝ ነገ ትመጭ ይሆናል ዛሬ ብትቀሪ!

እ ጠ ብ ቅ ሻ ለ ሁ!!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir