Get Mystery Box with random crypto!

ሄድሽ በቃ ልቤ ሲመፃደቅ እሷ አለች ብሎ ግን እየተሰማው አንድ አካሉ ጎሎ አመሻሹን ሲያመው | 💖የኔ ፍቅር 😘

ሄድሽ በቃ

ልቤ ሲመፃደቅ እሷ አለች ብሎ
ግን እየተሰማው አንድ አካሉ ጎሎ
አመሻሹን ሲያመው ልቤን እየዋለ
ካንቺ ፍቅር ሌላ አልቀበል አለ
አንድ ቀን ጠየኩት ልቤን በዝግታ
"ምንስ አስነካችህ ምንስ አሳስታ"
እሱ ግን አለፈኝ በአሳዛኝ ዝምታ
"በል አሁን ይብቃ አውጣት ቶሎ ብለህ
የፍቅሯን መቀነት ወደዚያ ጋ ጥለህ"
እርሷን ስለመርሳት ሳማክረው ውዬ
ንግግሬን ጨረስኩ አምስት ነጥብ ብዬ
አፉንም ከፈተ ነገረኝ ያለውን
አይኔ ያያት እለት የላከበት ጣሩን
እንዲህም አለ ጀመረ ወሬውን
"አይንህ እንዳስገባት ምን አለ ባወጣት
እርሳት ትለኛለህ ሳትጠብቅ ለከት
ምንሆንክ አንተማ ምንህስ ተነካ
ምኗን እንደወደድኩ አልገባህም ለካ
የውጪ ገፅታ ሀሰተኛ ውበት
የታዘለ በፊት ጠፊውን ደምግባት
አይደለም ለእሷ እኔ የምመኝላት
አለ እንጂ ከውበት በላይ ውበት
የተፈጠረች እለት የተሰጣት በገነት ፈጣሪዋን መምሰል ነው የሚያስብላት ውብ ናት
እግዚር መልካም ሆኖ መልካም እንዳረጋት
የተረዳችና የሆነችው ውብ ናት
እሷኮ ክብሯን የጠበቀች
እንደ ሌሎች ሴቶች ያልተገላለጠች
እቺን አጥቼማ እንዴት አላለቅስም
በብዙ ልቦች ፊት ቆሜ ማቅ አለብስም"
ልቤን ተረዳሁት ተናግሮ አበቃ በሲቃ
ግን ቆይ አንቺ........ሄድሽ በቃ


ማስታወሻነቱ ትተሽኝ ለሄድሽዉ

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir