ሴት ልጅ ባንተ ላይ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳዩ 7 ምልክቶች የማትወድህ የማትፈልግህ ሴት ጋር ሄ | 💖የኔ ፍቅር 😘
ሴት ልጅ ባንተ ላይ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳዩ 7 ምልክቶች
የማትወድህ የማትፈልግህ ሴት ጋር ሄዶ መጣበቅ አውሮፕላን ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው፡፡ መርከቧ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ መጥታ ልታገኛት እንደማትችል ሁሉ የማትወድህ የማትፈልግህ ልጅም እጅህ ልትገባ አትችልም፡፡ ስለዚህ አውሮፕላን ማረፊያ ቁጭ ብለህ መቼም የማትመጣዋን መርከብ ከመጠበቅ ይልቅ መርከቧ ወደምትመጣበት ወደብ መሄዱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡
ደስ ያለችህ የወደድካት ልጅ ከዚህ ቀጥለው ከተዘረዘሩት ምልክቶች በአብዛኛው ካሳየችህ ፍላጎት የላትም ማለት ነው፡፡
1. ካላስታወሰችህ
የሆነ ጊዜ የሆነ ቦታ ላይ ተዋውቃችሁ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስታገኛት ስምህን ከረሳችው አንተ ላይ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ ስምህ አበበ ሆኖ ሳለ በቀለ ብላ ከጠራችህም እንደዛው፡፡ ምክንያቱም ስምህን እንኳን አጥርታ ለማወቅ ያልፈለገች ልጅ አንተን ትፈልግሃለች ተብሎ አይታሰብም፡፡
2. ካልመለሰችልህ
ከአንድም ሁለት ጊዜ ስልክ ደውለህላት፣ ቴክስት አድርገህላት፣ ፌስቡክ ላይ ኢንቦክስ አድርገህላት፣ ኢሜይል ልከህላት ካልመለሰችልህ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ፍላጎት የላትም፡፡
3. በደምብ የማታወራህ ከሆነ
ከምትወዳት ልጅ ጋር ስትገናኝ ጥያቄዎች እያቀረብክ እሷ እንድታወራ በማድረግ ሁለመናህን ጆሮ አድርገህ እንድታዳምጥ ነው የሚመከረው፡፡ አንተም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን እየጠየቅህ ለማዳመጥ የመስማት የስሜት ህዋስህን ዘርግተህ ስትጠብቅ አጫጭር መልስ እየሰጠችህ ዝም የምትል ከሆነ ችግር አለ፡፡ ለጥያቄዎችህ አጫጭር መልስ ከመስጠት በተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጨዋታውን ለማራዘም ምንም አስተዋፅኦ የማታደርግ ከሆነ ኤርፖርት ላይ መርከብ እየጠበቅህ መሆንህን አውቀህ ኤርፖርቱን ለቀህ ወደ ወደቡ ተንቀሳቀስ፡፡
4. ድንገት እቸኩላለሁ ካለችህ
አግኝተሃት ደስ ብሎህ አብረሃት ቁጭ ብለህ ጨዋታ ስትጀምር ድንገት “እቸኩላለሁ” ብላህ ተነስታ ከሄደች እርምህን አውጣ፡፡
5. የማያሳምን ምክንያት የምትሰጥህ ከሆነ
ልታገኛት ልትጋብዛት ፈልገህ ስትጠይቃት የማያሳምን ምክንያት ነግራ እንደማይመቻት የምትነግርህ ከሆነ ፍላጎት የላትም፡፡ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ፊልም ሲመረቅ ልትጋብዛት ፈልገህ ጥያቄ ስታቀርብላት “በጣም ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን ዛሬ ማታ አባየ ቀዶ ህክምና ስለሚያደርግ ከእርሱ ጋር መሆን አለብኝ” የሚል አይነት ምክንያት ልትነግርህ ሲገባ “አይመቸኝም፡፡ ብዙ የሚታጠብ ሳህንና ድስት አለኝ” የሚል ዓይነት ምክንያት ከሰጠችህ ከአንተ ጋር አዲስ ፊልም ከማየት ይልቅ ቆሻሻ ሳህንና ድስት ማጠብ መርጣለች፡፡ ስለዚህ “አዲዮስ አሚጎ” ልትላት ይገባል፡፡
6. የምትደበቅ ከሆነ
መንገድ ላይ ስታይህ መንገድ የምትቀይር ከዛም አልፎ ለመደበቅ የምትሞክር ከሆነ ሁለተኛ እንዳታስባት እዛው ለራስህ ቃል ግባ፡፡
7. ሌሎች ምክንያቶች
ብዙ ጊዜ ልታገኛት ስትፈልግ “ቢዚ” ነኝ የሚል ምላሽ የምትሰጥህ ከሆነ፤ ስልክ ስትደውልላት “አሁን ማውራት አልችልም” እያለች የምታሳጥርብህ ከሆነ፤ በጨዋታችሁ መሀል በተደጋጋሚ ስለሌሎች ወንዶች የምታነሳብህ ከሆነ፤ ከሌሎች ሴት ጓደኞቿ ጋር ልታያይዝህ የምትጥር ከሆነ፤ ፍቅረኛ የመያዝ ፍላጎት እንደሌላት ከነገረችህ ካንተ ጋር የፍቅር ግንኙነት የመጀመር ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው፡፡
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
#Share
@Yenefekir
@Yenefekir