ስልክ ቁጥር የመቀበል ጥበብ ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር መቀበልና ከአውሮፕላን በፓራሹት መዝለል አን | 💖የኔ ፍቅር 😘

ስልክ ቁጥር የመቀበል ጥበብ

ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር መቀበልና ከአውሮፕላን በፓራሹት መዝለል አንድ ናቸው፡፡ መቶ ጊዜ ከአውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ የመዝለል ልምድ ቢኖርህም ለመቶአንደኛ ጊዜ ስትዘል መፍራትህ አይቀርም፡፡ ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር ስትቀበልም ተመሳሳይ ነው፡፡ አስር ሺ የሴቶች ስልክ ቁጥር የያዘ ማውጫ መጽሐፍ (ዳይሬክተሪ) ለማሳተም የአንዲት ሴት ስልክ ቁጥር ቢቀርህ እንኳን አንዷን ስልክ ቁጥር ለማሟላት ወደ አዲስ ሴት ስትራመድ ልብህ ድው ድው ማለቱ አይቀርም፡፡ ከአውሮፕላን ስትዘል የሚያስፈራህ የመከስከስ አደጋ ሲሆን ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር ለመቀበል ስትራመድ የሚያስፈራህ ደግሞ “እምቢ ልትለኝ ትችላለች” የሚል ስጋት ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል?

1. ልብ በል… ጨዋታው ጣፍጦህ ተንከርፍፈህ እስክትሰለች ድረስ ካወራሃት፣ የመለማመጥ ስሜት ካሳየህ፣ ከተርበተበትክ ስልኳን የማግኘት እድልህ ከዜሮ እስከ እጅግ በጣም በጣም አነስተኛ ድረስ ይሆናል፡፡

2. ደስ የምትልህን ሴት ቀርበህ ማነጋገር፣ መተዋወቅና ስልክ ቁጥር መቀበል ወደ ጦር ሜዳ እንደመዝመት አድርገህ አትየው፡፡ ቀለል አድገው፡፤

3. አያቶቸህ ምናልባት ወላጆችህ የሞባይል ስልክ፣ የቴክስት፣ የኦንላይን ዴቲንግ፣ የፌስቡክና የትዊተር ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ጊዜ ተዋውቀው ተቀጣጥረው ተፋቅረው መርፌና ክር ሆነው አንተን ወልደዋል፡፡ አንተ በዚህ ሁሉ የዘመኑ ቴክኖሎጂ እየታገዝክ የህይወትህ ውበትና ጣዕም የምትሆን ሴት እንዴት ማግኘት ያቅትሃል? በል ተንቀሳቀስ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
💖የኔ ፍቅር 😘

💖የኔ ፍቅር 😘

@yenefekir
8.31K ተመዝጋቢዎች
ብሎጎች ምድብ
🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓. ❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤. ❤ HBD ለማለት፤ 🎂. ❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ...