Get Mystery Box with random crypto!

#Fekir_1K251 ።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር ።።።።።። ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር | 💖የኔ ፍቅር 😘

#Fekir_1K251

።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር ።።።።።።

ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር
እንዴት አትበሉ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ብታውቁ ምንም ላይጠቅማችሁ
አጠይቁኝ እኔን ትላንትስ ብላችሁ
ታሪኬን የዃሊት እያስታወሳችሁ
የት ነበርሽ አትበሉ አታብዙ ጥያቄ
የትስ እንደነበርኩ እኔ የት አውቄ
ምላሼን በመሻት ጥያቄ አታብዙ
ዃላ ብነግራችሁ ብዙ ነው መዘዙ
አታድሙት ቁስሌን በሾክ ወጋግታችሁ
የማያባራ ደም ጉድ እንዳይሰራችሁ
ዝምታዬ ጎልቶ  ስሜት ካልሰጣችሁ
አላደክምም ራሴን አንዱም ላይገባችሁ

ስለዚህ እባካችሁ።።።።።።።

አጠይቁኝ ይቅር የለኝም መልሳችሁ።
 
@yenefekir
   ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌