Get Mystery Box with random crypto!

የሌባው የፍቅር ደብዳቤ . ይድረስ ለውዷ ልቤን ለሰረቀችኝ ሌባዬ ሰላምታዬን ከአንቺ ሲደርስ ጤና | 💖የኔ ፍቅር 😘

የሌባው የፍቅር ደብዳቤ
.
ይድረስ ለውዷ ልቤን ለሰረቀችኝ ሌባዬ
ሰላምታዬን ከአንቺ ሲደርስ
ጤናሽና እድሜሽን እንዲያራዝመው በመመኘት
ነው። ውዴ አንቺ ልብ ውስጥ መግባት ሰው ኪስ ውስጥ
እንደ መግባት ቀላል
እንዳልሆነ ባውቅም እንደ ፖሊስ ዱላ ናፍቆትሽ
አካሌን ቢጎዳውም አንቺን
ማሰብ ዛሬም አላቆምኩም
በእርግጥ ጸባይሽ እንደ አቃቢ ህግ መስቀለኛ ጥያቄ
ግራ ቢያጋባኝም..
ዛሬም ትናፍቂኛለሽ የኔ ፍቅር
አውቃለሁ በዚህ ዘመን ለፍቅር መታመን ከማረሚያ
ቤት እንደማምለጥ ቢከብድም እኔ ግን ዛሬም ባንቺ ያለኝ
እምነት አልተሸረሸረም
አንቺ ፊት መቅረብ ማለት እኮ ልክ የሞት ፍርድ
ሊሰጥበት የቀረበ
ሰው ይመስል ገና ሳይሽ ልቤ ግራ ኪሴ ውስጥ ይገባል
የኔ ፍቅር መርማሪ ፖሊስ ይመስል የሆነውንም
ያልሆነውንም አወራሁ
አይደል ለማንኛውም እስከምንገናኝ ሰላሙን
እመኝልሻለሁ። ..........................
ያንቺው ሌባ ይድረስ ልቤን ለሰረቀችው


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir