Get Mystery Box with random crypto!

ነብዩሏህ_ኢብራሂም_(ዐ,ሰ) ክፍል ብዙም ሳይፈልጉት ነበር ኢብራሂምን አግኝተ | የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች

ነብዩሏህ_ኢብራሂም_(ዐ,ሰ)

ክፍል

ብዙም ሳይፈልጉት ነበር ኢብራሂምን አግኝተው ለፍርድ ያቆሙት።
ዳኛውም፦"ይህን አሳፋሪ ተግባር በአማልክቱ የፈፀምከው አንተ ነህ እንዴ?"
ኢብራሂም፦"አረ እኔ አይደለሁም ይሄ ትልቀኛው ነው እሱም ጠይቁት
እንጂ...በዛ ላይ ፋስ ተሸክሟል እራሱ ነው የፈጃቸው።ከፈለጋችሁ
ጠይቁት"አላቸው።
ህዝቡ፦"እንዴት መናግር እና መስማት የማይችልን ጣኦት ጠይቁት ትላለህ!!!"
ኢብራሂም፦"አያችሁ መናገር እና መስማትን የማይችሉ ጣኦታትን ነው
እያመለካችሁ ያላችሁት።ግን ትንሽ አታስተነትኑም!!!"
ኢብራሂም እችን ሲናገር ሁሉም ጥፋት ላይ መሆኑን ተረድቶ ቀዘቀዘ።ነገር ግን
ሸይጣን አስውቦ ገለፀላቸውና ወደ ጥመታቸው በመመለስ ኢብራሂምን
ለሰራው ቅጣት ይሆን ዘንድ በእሳት ለማቃጠል ትዕዛዝ አስተላለፉ።
አሁን ኢብራሂምን ለማቃጠል ማገዶ ለቀማ ተጀምሯል...እያንዳንዱ ነገድ
በርካታ ማገዶ እንጨቶችን ሰብስቦ መከመርም ጀምሯል።
በመጨረሻም ኢብራሂምን ለማቃጠል የተከመረው የእንጨት ብዛት ትልቅ
ተራራን አከለ።ከተለያዩ አጎራባች ሀገራት የኢብራሂምን አስከፊ እና ዘግናኝ ቅጣት
ለመመልከት ወደ ባቢሎን ከተማ ሰዉ መጥቷል።
እሳቱ መቀጣጠል ሲጀምር የእሳቱ ነበልባል በሰማይ በራሪ አዕዋፋትን
እየጠበሰ ይጥላቸው ነበር።እንግዲ በዚህ ውስጥ አሁን ኢብራሂም ሊገባ
ነው።
እሳቱ በጣም ከተፋፋመ በኋላ አይደለም ኢብራሂምን ለማስገባት ይቅርና ራቅ
ብሎ እንኳን ወደ እሳቱ ድንጋይ ለመወርወር ነበልባሉ አይሰጥም ነበር።
ይህን ግዜ ሸይጣን በሰው ተመስሎ መጣ'ና አንድ መፍትሄ ሹክ
አላቸው።እሱም መስፈንጥር በመጠቀም ኢብራሂምን ወደ እሳቱ ማስፈንጠር
እንዳለባቸው ነገራቸው።
ከዚያም ያ የተባለው መስፈንጥር ተዘጋጀ'ና ኢብራሂምን ወደ እሳቱ
ለመወርወር ማስፈንጠሪያው ላይ አስቀመጡት።
ልክ ኢብራሂም እዛ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ጂብሪል መጣ'ና፦"ምትፈልገው ነገር
ካለ እኔ ልርዳህ...ከፈለግክም እሳቱን ላጥፋልህ" አለው።
ኢብራሂምም፦"አይ ዛሬ እርዳታን ከአላህ ብቻ ነው ምፈልገው" ብለው
መለሱለት።
በመስፈንጥሩ ኢብራሂም ወደ እሳት ሲወረወር እዛ የተሰበሰበው ህዝብ
ሁላ፦'እሳት ትገባላችሁ እያለ ይዝትብን የነበረው ሰውዬ ቀድሞ እራሱ ገባ
አይደል!!"እያለ ማላገጥ ጀመረ።
ነገር ግን በአላህ ልዕልና እና በሁሉ ነገር ቻይነቱ እሳትን፦"አንች እሳት ሆይ!!!
ኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ እና ሰላም ሁኚለት" በማለት ትዕዛዙን አስተላለፈ።
ከረጅም ርቀት በማስፈንጠሪያ ወደ እሳቱ የተወረወረው ኢብራሂምም ልክ
እሳቱ ውስጥ ሲገባ ከላይ እሳት ሆኖ የታየው ውስጡን እንደ ጀነት ሆኖ
አገኘው።
እሳቱ ተፋፍሟል ህዝቡ በደስታ እራሱን አያውቅም።በመጨረሻም እብራሂም
ሞቷል ብለው ሁሉም ተበታተኑ እሱቱ ግን ይባስ እየተፋፋመ ነው።
የኢብራሂም እናት ቁጭ ብላ የልጇን መጨረሻ በመጠባበቅ ላይ ሳለች ድንገት
ከነበልባሉ ውስጥ ልጇን ኢብራሂምም ተመለከተች።
ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦"ኢብራሂም....እኔ ወደንተ ልመጣ እፈልጋለሁ ጌታህን
ለምንልኝ'ና አንድ ግዜ ልምጣ" አለችው።
ኢብራሂምም መንገድ እየጠቆማት፦"ነይ በዚህች በኩል" አላት።
እሷም እየፈራች ትንሿን መንገድ ይዛ ወደ ልጇ ገሰገሰች።መሀል ከደረሰች
በኋላም እሳቱ ሲንቀለቀል ስታይ፦"ኢብራሂም ፈርቻለሁ"አለችው። (ወይ
እናት!!!)
ኢብራሂምም፦"እናቴ እሳቱ እኮ አያቃጥልም ዝም ብለሽ ነይ" ሲላት እሳቱ
መሀል ደረሰች'ና ያብራኳን ክፋይ በእቅፏ አስገባችው።
በሁለት እጆቿ አቅፋው እየሳመችው ፊቱን ትጠራርግ'ና ዳግም ወደ እቅፏ
ታስገባዋለች።ለተወሰኑ ሰዐታት አብራው ካሳለፈች በኋላ ኢብራሂምም ወደ
ህዝቧ እንድትመለስ ያዝዛትና ለመመለስ ስትሞክር እሳቱን ይበልጥ ተፋፍሞ
አገኘችው።
ወደ ልጇ ዞራም፦"ልጄ በጌታህ ይሁንብህ ጌታህን ለምንልኝ'ና
አሳልፈኝ"አለችው።ኢብራሁምም ዱዓ አደረገና እናቱን እንድትሻገር
አደረገ።እናትየውም ልክ የእሳቱን መውጫ ጫፍ ላይ ስትደርስ፦"ልጄ ሰላም
ሁን" ብላው ወጣች።
በነጋታው የከተማይቱ ነዋሪ እሳቱ ጋር መጥተው ሲያጣሩ እሳቱ እንደነበር ነው
ምንም አልቀነሰም።በዚህ ሁኔታ ኢብራሂም ለ40 ቀናት እሳት ውስጥ አሳለፉ።
በመጨረሻም እሳቱ ሲጠፋ ህዝቡ ግር ብሎ መጣ።በዚህ አጋጣሚ ነበር
ኢብራሂም ከመጀመሪያ ውበቱ 70 እጥፍ ጨምሮ ከእሳቱ ሲወጣ
የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ሸይጣን መስሎት ኡኡኡ....ያለው።
ኢብራሂም ሲከተላቸው እነሱ ሲሸሹ ሩቅ ከተጓዙ በኋላ አላህ እሱን አድኖት
እነሱን አጠፋቸው።የኢብራሂም በእሳት 40 ቀን ቆይቶ በሰላም የመውጣቱ
ነገር በተለያዩ ሀገራት ለአመታት የሰው ልጆች መነጋገሪያ ሆኖ ከረመ።
ኢብራሂም ምንም እንኳን የዳዕዋ ጥሪያቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም ሳራ
እና ሉጥ ከተባሉ ሁለት ሰዎች በላይ ተከያይ ሊያፈሩ አልቻሉም ነበር።
ኢብራሂምም ሚስቱ ሳራን እና ሉጥን ይዞ ወደ ሌላ ሀገር ለመሰደድ
ወሰነ።ከባቢሎን ምድር ብዙ ተጉዘው ፊለስጢን ደረሱ።
በዚያ ዘመን ፊለስጢንን የሚያስተዳድረው የግብፅ ንጉስ ነበርና ሳራ የምትባል
በጣም ቆንጅዬ ሴት በግዛቱ ውስጥ እንደምትገኝ በወሬ ደርሶት ወታደሮቹ
እሷንም አብሯት ያለውንም ሰው እንዲያቀርቡለት አዘዘ።
ሁለቱም በወታደሮች ተከበው ወደ ቤተ መንግስት በመሄድ ላይ ሳሉ አንድ ነገር
ተመካከሩ።ኢብራሂም ባሏ ነኝ ብሎ ከተናገር ስለሚገድሉት ወንድሟ ነኝ ሊል
ወሰኑ። ሌላው የአላህ ስራ ነው ብለው ኢብራሂምን ወደ እንግዳ ማረፊያ
አስገብተው ሳራን ለንጉሱ አሳልፈው ሰጡ።
ኢብራሂምም ምኗ ነህ ተብሎ ሲጠየቅ ወንድሟ ብሎ በመመለሱ ከሞት
ተርፏል።አሁን የሳራ እንግልት ከወደ ውስጥ በኩል ጀምሯል....ንጉሱ
ሊተናኮላት ሲሞክርም፦"ጌታዬ እኔ ባንተ ያመንኩ ስሆን ከመጥፎ ነገር ሁሉ
ባንተ እጠበቃለሁ። ይህንንም ንጉስ እኔ ላይ ስልጣን አትስጠው" እያለች
አላህን ተማፀነችው።
ንጉሱም እጁን ወደ ሳራ ሲዘረጋ እዛው በዘረጋበት እጁ ደርቆ ቀረ።ያን ግዜ
ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር ሳራም ይህ ንጉስ ከሞተ ወታደሮቹ
እሷንም እንዷይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው።
አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ፀያፍ ተግባር
አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....
ሳራም እንደመጀመሪያው ጌታዋን ተማፀነች።የንጉሱ እጅም በቦታው ደረቀ።
ያን ግዜ ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር አሁንም ሳራም ይህ ንጉስ
ከሞተ ወታደሮቹ እሷንም እንዳይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው።
አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ውዳቂ ተግባር
አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....
ይህን ግዜ አላህ የንጉሱን መላ ሰውነት ፓራላይዝድ አደረገው።ንጉሱም
ዳግም ላይተናኮላት ቃል ገብቶላት አላህም ለቀቀው።
ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ሰው ናት ብላችሁ ሸይጣን ታመጡልኛላችሁ
እንዴ!!! በሉ አንድ አገልጋይ ስጧት'ና ከዚህ አስወጡልኝ" አላቸው።
አሁን እነኢብራሂም ሁለት ሆነው የገቧትን ከተማ ከአገልጋይቱ ሶስት ሆነው
ወጡ። በነገራችን ላይ ሳራ ምንም እንኳን ቆንጂት ብትሆንም መውለድ
ማትችል(መሀን) ነበረች።
ኢብራሂምም እድሜውን ዳዕዋ ላይ ብቻ በማሳለፍ እድሜውን ፈጅቶ
ሸምገልገል ብሏል።ሳራ አንድ ቀን ኢብራሂምን፦"አንተ እድሜህ ገፍቷል እኔም
እንደምታየው መውለድ አልቻልኩም።ስለዚህ ይህችን አገልጋያችንን አግባት'ና
ልጅ ውለድ" አለችው።
ኢብራሂምም፦"ተይ ተይ...ሳራ እኔ እሷን ባገባ ትንሽ ቅናት ቢጤ ሊያገኝሽ
ይችላል።በተለይ ደሞ ልጅ ስንወልድ...እኔ ደሞ አንችን ምንም እንዲከፋሽ
አልፈልግም" ብሎ መለሰላት።
ምንም እንደማይፈጠር አሳምናው በዚህም በጣም......