Get Mystery Box with random crypto!

ው...!! !መልሱልኛ ማውራትም አትችሉም እንዴ!!' አላቸው። ምንም ሚመልሱት ነገር የለም። በእጁ | የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች

ው...!!
!መልሱልኛ ማውራትም አትችሉም እንዴ!!" አላቸው።
ምንም ሚመልሱት ነገር የለም።
በእጁ በያዘው ፋስ እያንዳንዱን የድንጋይ እና የእንጨት ቅርፃ ቅርፅ ብትንትኑን
አውጥቶ አንድ ትልቁን ጣኦት ብቻ ተወው'ና ሌሎች ጣኦታትን የቆረጠበትን
ፋስ በትልቀኛው ላይ አሸክሞ ሰዉ ከተሰበሰበበት ሳይመጣ ኢብራሂም ቤተ
አምልኮውን ትቶ ወጣ።
ህዝቡ ገና ከተማ ከመግባቱ አማልክቱ ጋር ሊሳለም ሲገባ ሁሉም አይናቸውን
ማመን እስኪያቅታቸው ድረስ ያዩት ነገር አስደነገጣቸው።
ህዝቡ ባጠቃላይ ክፉኛ ተቆጣ...ይህን ተግባር የተገበረውንም ሰው አይቀጡ
ቅጣትንም ለመቅጣት መዛት ጀመሩ።ግን ነገሩን በጥልቀት ሲመረምሩት
ከኢብራሂም ሌላ ማንም እንዲህ ሊያደርግ እንደማይችል በመገመት
ኢብራሂምን ለፍርድ ለማቅረብ ፍለጋ ተጀመረ.....

ክፍል ኢንሽአላህ ይ.....ቀ......ጥ.......ላ........ል፡፡
@yenebiyattaric
@yenebiyattaric